የሐገር መልክ
#Ethiopia | የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን የሕይወት ታሪክ የያዘ አዲስ መጽሐፍ በታሪክ ተመራማሪው ኸድር ታጁ አዘጋጅነትና በቤተሰቦቻቸው ድጋፍ ታትሞ ለንባብ ሊበቃ ነው።
"የሐገር መልክ" በሚል የተሰየመው ይኸው ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ተቀዳሚ ሙፍቲ በሕይወት እያሉ የተጀመረና እሳቸው በሚገኙበት መድረክም ይመረቃል ተብሎ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።
በመጨረሻም ከውልደት እስከ ህልፈተ-ሕይወታቸው ድረስ ከዚህ ቀደም ለአደባባይ ያልበቁ በርካታ ገጽታዎቻቸውንና የታሪክ መረጃዎችን ያካተተ ሙሉ መጽሐፍ ሆኖ ለአንባቢያን መዘጋጀቱን አዘጋጁ ኸድር ታጁ በተለይም ለየኑስ ሚዲያ ገልጿል።
August 23, 2026 46