ከነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ባህርያት
***
41. ለሴትም ሆነ ለወንድ፤ በዕድሜ ለገፉ ሰዎች፣ ህፃን ልጅም ይሁን ጎልማሳ ላናገራቸው ሁሉ ይቆማሉ፡፡ ያማከራቸውን ያማክራሉ፡፡
42. ተናጋሪ ንግግሩን ሳይጨርስ አይናገሩም፡፡ እጃቸውን የያዛቸው ሰው እስካልለቀቃቸው ድረስ ቀድመው አይለቁም፡፡
43. አንድ ሰው ከርሳቸው አንዳች ነገር የፈለገ እንደሆነ ሳይሰጡት አይመልሱትም፤ የሌላቸው ቢሆን እኳ ከሰሓቦቻቸው ይጠይቁለታል፡፡
44. በሐቅ ጉዳይ ላይ ማንኛውም ሰው፤ ደካማም ይሁን ጠንካራ፤ ድሃም ሆነ ሀብታም እርሳቸው ዘንድ እኩል ነው፡፡
45. አቀማመጣቸው የትዕግስት እና የታማኝነት አቀማመጥ ነው፡፡
46. እርሳቸው ዘንድ ይበልጥ ደረጃ ያለው ሰው፤ ይበልጥ አላህን የሚፈራ ነው ።
47. ባህሪያቸው ለሁሉም የሚመች ገር ነው።
48. አቀራረባቸው ለረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቅ ሰው ነው፡፡
49. ማህበራዊ ኑሮአቸው ልስላሴና መግባባት የተሞላበት ነው፡፡
50. ተራግመው አያውቁም፣ አያማርሩም፣ አይጮሁም፣ የሚያነውሩና የሚያጥላሉ አይደሉም፡፡
51. ሰዎችን ባጠፉ ጊዜ መምከርና ማስተማር የፈለጉ እንደሆነ በቀጥታ ስማቸውን በመጥራት ሳይሆን ጥፋቱን በማንሳት ‹ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው እንዲህ እንዲህ የሚያደርጉት› ይሉ ነበር፡፡
52. ቀልድ አያበዙም፡፡ ይቀልዳሉ፣ ነገርግን ሐቅን እንጂ አይናገሩም፡፡
53.ከማይፈልጉት ነገር ችላ ያሉ ናቸው፡፡ አያስቡትም፣ አይከተሉትም።
54. አላህ የመረጠላቸውን ነገር ይመርጣሉ፡፡ በመረጠላቸው ነገርም ይረካሉ ።
55. አንድንም ሰው ዘልፈውም ሆነ በድለው አያውቁም፡፡ የጎዳሁት ሰው ካለ ዛሬውኑ ካሳውን ይቀበለኝ ይሉ ነበር፡፡
56. የሰዎችን ገመና አይከታተሉም፡፡ ሰዎች ከሰዎች ይልቅ ወደራሳቸው ችግር እንዲመለከቱ ይመክሩ ነበር፡፡
57.ሲናገሩ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች በራሳቸው ላይ ወፎች የተቀመጡ በሚመስል መልኩ በጥሞና ያዳምጧቸዋል፡፡
58. ባልደረቦቻቸው እርሳቸው ዝም ሲሉ ብቻ ጠብቀው ይናገራሉ፡፡
59. ሰሓቦቻቸው በሚስቁት ይስቃሉ፡፡ እነርሱ በሚደነቁት ነገር ይደነቃሉ፡፡
60.*ንግግር ለማይችል አላዋቂንም ባላገር/ዘላን ሰውን ይታገሳሉ፡፡
61.ከአንድም ሰው ሙገሳን የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ የሚኖሩትም ሆነ የሚሰሩት ለአላህ (ሱ.ወ.) ነው፡፡
62. ሰዎችየዒልም (ዕውቀት) ባለቤቶች ዘንድ እንዲያርፉ፣ ከዕውቀት ማዕድም እንዲቋደሱ ይመክራሉ፡፡
63.አንድ ሰው ቢቆጥር የተናገሩትን ቃላት መቁጠር በሚችል መልኩ ነው የሚያወሩት፡፡ ንግግር አያበዙም፡፡
64. ሲናገሩ የሚሰማቸው ሁሉ ለረዳቸው በሚችል መልኩ ይናገራሉ፡፡
65. ለንግግር ማሳመርም ሆነ ለመምሰልና ለማስመሰል አይጨናነቁም፤ አይፈላሰፉም፡፡
66. አድማጭ ይረዳቸው ዘንድ ንግግራቸውን ሶስቴ ይደጋግማሉ፡፡
67.ረጋ ባለና ግልጽ በሆነ መልኩ ይናገራሉ፡፡
68.ሲናገሩም ሆነ ቁርኣን ሲያነቡ ድምፃቸው ውብ ነው፡፡
69. ከልጆች ጋር ይቀልዳሉ፡፡ ህፃናትን ያጫውታሉ፡፡ 70. ሕፃናት ልጆችን ተሸክመው ይሰግዳሉ፡፡
70. ለባልደረቦቻቸው ስኬትንና በረከትን ይለምናሉ፡፡
71. ቁርኣን ሲነበብ ከሌላ ሰው መስማት ይወዳሉ፡፡
72. በግመላቸው ላይ ሆነውም ጭምር ቁርኣን ያነቡ ነበር፡፡
73. አካሄዳቸው ያማረና ፈጠን ያለ ነው፡፡ ሲራመዱ ምድር የምትጠቀለልላቸው ይመስላሉ፡፡
74. ሲፀዳዱ ስውር ስትር ብለው ከሰዎች ዓይን ርቀው ነው፡፡
75.,መዓዛቸው እጅግ ያውዳል፡፡ ላባቸው እንደሚስክ ይሸታል፡፡
76. እጅግ መልካም ሰው፣ እጅግ ለጋሽና እጅግ ጀግና ናቸው፡፡
77. እጅግ በሳልና አዋቂ፤ አቻ የሌላቸው ብልሃተኛም ናቸው፡፡
78. ሲመፀውቱ ድህነትን የማይፈራ ዓይነት ሰው መመጽወትን ይመፀውታሉ፡፡
79. ለሻጭ መብት ይሠጣሉ። በመሸጥና ባለመሸጥ መካከል አማራጭ ያቀርቡለታል፡፡
80. ከአንዱ ወንድማቸው ሊበድሩ ይችላል፡፡ ንብረታቸው በዕዳ የሚያዝበት ሁኔታ ይኖራል።
https://t.me/Nejashipp
Telegram
Nejashi Printing Press
ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።

August 22, 2026 4.6K 36