እቴ ሲዘገዩ የሰበሩት ሹሎ ያረገፉት በቅሎ የገፉት በርትቶ የጣሉት ተነስቶ የሳሳ ደንድኖ የታመመም ድኖ የናፈቀ… — NK's Journal — TG.ME

እቴ ሲዘገዩ

የሰበሩት ሹሎ
ያረገፉት በቅሎ
የገፉት በርትቶ
የጣሉት ተነስቶ
የሳሳ ደንድኖ
የታመመም ድኖ
የናፈቀ ረስቶ
የወደደም ጠልቶ


እንደሚጠብቆት ያውቃሉ?

ዳሩ  ቢሆንም
እሜቴ እንጠብቆታለን....

ግና ሲዘገዩ
እንደድሮው የለም ...
ከሰሜን ከደቡብ
ከነፈሰዉ ነፍሰን...
በአንዲት ገላ ላይ
ሌላ ሌላ ሆነን...
እቴ ሲዘገዩ
እንጠብቆታለን

እቴ ባይዘገዩ😊

🖊️ Dr. Abdu, GP
(@beautifulminds1)

@nks_journal
😁6🥰3
August 27, 2026 556 1