[1] ሰለፍዮች ፡ ረሱል ﷺ መውሊድን አልሰሩትም ለምን ትሰራላችሁ? ብለው አህባሾች ሲጠየቁ እነሱ የመለሱት መልስ ከስር ባለው ሊንክ ተመልከቱ ‼️👇
https://t.me/Mistre_ahbashe/7121?single
[1] አንደኛ ላይ የጠቀሱት ብዥታ
የዓኢሻ ረዲየላሁ አንሃ ንግግር ነው እሱም ፡
كان رسولُ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم لَيدَعُ العمَلَ
وهو يُحِبُّ أنْ يعمَلَ به خشيةَ أنْ يعمَلَ به النَّاسُ فيُفرَضَ عليهم
« ረሱል ﷺ አንድን ስራን መስራት እየወደዱ ይተዉ ነበር ሰዎች ሰርተውት ግዴታ እንዳይሆንባቸው በመፍራት »
እንግዲህ ተመልከቱ ሀዲሱ እየተናገረ ያለው ረሱል ﷺ አንድ የሚሰሩት ስራ አለ ያ ስራ ደግሞ ዋጂብ ሳይሆን የተወደደ የሆነ ስራ ነው እሱን ስራ ኡማቸው ላይ ግዴታ እንዳይሆንባቸው በመፍራት ይተዉታል ።
እንደነሱ አካሄድ ከሆነ ከዚህ ሀዲስ የምንረዳው ረሱል ﷺ መውሊዳቸውን አክብረው ከዛ ኡማቸው ላይ ግዴታ እንዳይሆን ትተውታል ነው ስለዚህ በአጭሩ እንጠይቅ
አንደኛ ፡ ረሱል ﷺ የቱ ጋር ነው ያከበሩት?
ሁለተኛ ፡ እኛ ሰለፍዮች ቁርዓን እና ሀዲስን የምንረዳው -ሁል ግዜ እንደምንለው - በቀደምቶች አረዳድ ነው ስለዚህ ቀደምቶች ይህን ሀዲስ እንደ እናንተ ተረድተው ተርጉመዋሉ !? ተርጉመዋል ካላችሁ ሀያ መረጃ ስጡን !!
ሶስተኛ ፡ ረሱል ﷺ ግዴታ እንዳይሆንብን መውሊዳቸውን ጭራሹንም አላከበሩም ምትሉን ከሆነ ታድያ ሰሃባዎች ለምን አላከበሩትም ማክበርም ነበረባቸው ለምሳሌ ረሱል ﷺ ተራዊህ ግዴታ እንዳይሆንብን ብለው ትንሽ ቀን አሰግደው ትተውት ነበር ከዛ ረሱል ﷺ ከሞቱ በኋላ ግዴታ ይሆናል ተብሎ የሚሰጋው ነገር ተቋረጠ ያን ግዜ ሰሀባዎች ተራዊህን በጀማዓ ሰግደዋል መውሊድንስ ለምን አላከበሩም !?
እነዚህን ሶስት ጥያቄዎች በዚህ ሀዲስ የገነባችሁትን ጨለማ ያፈራርሰዋል ‼️ ያለ ምንም ማፈንገጥ ቀጥታ መልሱልን ‼️[2] ሁለተኛ ላይ የጠቀሱት ብዥታ
መውሊድን ረሱል ﷺ ባይሰሩትም እኛ እንሰረዋለን አይነት ነው ሱብሀነላህ ‼️
ከመሰረቱ ውድቅ እና የጀህል ንግግር ነው
فمن رغب عن سنتي فليس مني
ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል ፡ « ከኔ ሱና ውጭ ያፈነገጠ ከኔ አይደለም »ብለዋል
ታድያ እነዚህ ሰዎች እኛ ከ ረሱል ﷺ ሱና ሌላ ይሸለናል እያሉ ይገኛሉ ሱብሀነላህ ‼️አላህ ከዚህ እውርነት ይጠብቀን ‼️
እንደዚህ እንዲሉ ያነሳሳቸው አንድ ሀዲስ አለ ሀዲሱን ባለማወቅ ይሁን ወይም እያወቁ ከመጥመም ይሁን ባናውቅም ሀዲሱን ዑለማዎች ከተረዱበት ባፈነገጠ መልኩ የተረዱ ይመስላሉ ፡
ሀዲሱ እንዲህ የሚል ነው :
مَا رَأَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُصَلِّي سُبْحَةَ الضُّحَى قَطُّ، وَإِنِّي لَأُسَبِّحُهَا،
ዓኢሻ ረዲየላሁ አንሃ እንዲህ ትላለች ፡
« ረሱል ﷺ ን ሰላተ ዱሀን መቼም ሲሰግዱ አልተመለከትኩም እኔ ግን እሰግዳለው »
እንግዲህ ተመልከቱ ሀዱሱን ዑለመዎች የተረዱበትን እና እነዚህ ሰዎች የተረዱበትን
በነገራችን ላይ ዓኢሻ በዱሃ ሰላት ዙሪያ ፡ ሶስት አይነት ዘገባዎች አሏት ፡ አንደኛ ፡ በልቁ አልሰሩትም የሚል ነው ሁለተኛ ከሰፈር ሲመጡ እንጂ አይሰግዱም ነበር የሚል ነው ሶስተኛ ፡ በልቁ ይሰግዱ እንደነበር አስተላልፋለች ሶስቱንም ሀዲስ ኢብን ሀጀር ቡሉግ ላይ ጠቅሷቸዋል
እነዚህን ሀዲስ ዑለማዎች እንዴት አስማሙት !!
ሙባረካፉሪይ ቡሉግ ሸርሃቸው ላይ ከተናገሩት ውስጥ :-
قال المباركفوري ؛ وفعلها مع عدم رؤيتها من النبي صلى الله عليه وسلم إما لأنها علمت فضائلها من قول النبي صلى الله عليه وسلم أو بلغها فعله صلى الله عليه وسلم لها فإن عدم رؤيتها لا يستلزم عدم الفعل مطلقا ...
بلوغ المرام مع تعليقه إتحاف الكرام ص ١٢٤
[1] ሰፊዩ ራህማን ሙባረከፉሪይ እንዲህ ይላሉ :-
« ከነብዩ ﷺ (የዱሃን ሰላት)ሳትመለከት መፈፀሟ ፡ ወይ ከነብዩ ﷺ ንግግር ትሩፋት መኖሩን አውቃ ነው ወይም የነብዩ ﷺ (የዱሃን ሰላት) መስራታቸው ደርሷት ነው :: (ስለዚህ) እሷ (ረሱል ﷺ ሲሰግዱ ) አለመመልከቷ ያስራ በልቁ አልሰሩትም የሚለውን አያስይዝም ... »
[2] ቃዲ ዒያድም ዓኢሻ የዘገበችውን ሁለት ሀዲስ ሲሰበስብ እና ሲያስማማ ይህን ሀዲስ ማለትም « ሰላተዱሃን ሲሰግዱ አላየውም » የሚለውን ሀዲስ ከጠቀሰ በኋላ እንዲህ ይላል :-
« በዚህ ንግግሯ እና « ይሰግዱ ነበር » በሚለው ንግግሯ ስንሰበስብ ፡
(ሲሰግዱ አላየውም) ብላ ተናግራ ያወገዘችው አለማየቷን ሲሆን (ሰግዷል) ብላ ያረጋገጠችው ደግሞ ከሌላ (ሰሃባ) አንስታ ነው »
[ ፈትሁል ባሪ 3/17 ]
[3] ሙሂቡጠበሪይ ፡
[1]« ከሰፈር ሲመጡ እንጂ ዱሃን አይሰግዱም ነበር » በሚለው ሀዲስ እና [2] « አራት ይሰግዱ ነበር አላህ የሻላቸውንም ይጨምሩ ነበር » ሚለው ሀዲስ እንደሚስማማ አውርተዋሉ ፡ (እሱም)
የአንደኛው መስጅድ ላይ በመስገዳቸው ይፈሰራል
ሁለተኛው ፡ ደግሞ በቤት በመስገዳቸው ይፈሰራል[¹]
የሚረብሸው ሶስተኛው ሀዲሷ ነው ማለትም « ረሱል ﷺ የዱሃን ሰላት ሲሰግዱ አላየውም እኔ ግን እሰግዳለው » ለዚህም መልስ ተሰቶታል (እሱም ፡ ሲሰግዱ አላየውም ብላ ) ያወገዘችው የተለየ ሁኔታ ያለውን ሰላት ነው ( ለምሳሌ ፡ ዱሃ ላይ ስምንት ረከዓ መስገድ ይመስል )
እንደዚህ ማስማማቱን ከኢብን ሂባን ነው የወሰደው
[ ፈትሁል ባሪ 3/67 ]
[¹] ( ማለትም ፡ አንደኛ ላይ ያለው መስጂድ ላይ ከሰፈር ሲመጡ እንጂ አይሰግዱም በሚለው የሚፈሰር ሲሆን ሁለተኛ ቤት ውስጥ አራት ይሰግዱ ነበር አላህ የሻላቸውንም ይጨምሩ ነበር በሚለው ይፈሰራል)
|| ሌሎችም ከነዚህ ጋር በሚመሳሰል መልኩ አስማምተውታል ለምሳሌ :- ሸውካኒ ነይሉል አውጣር 3/65 ላይ እንዲሁም ኢብን ሀጀር ፈትሁል ባሪ 3/67 ላይ መመልከት ይቻላል ።
|| እንግዲህ ተመልከቱ የነዚህን የተንሻፈፈ አገነዛዘብ እና የዑለማዎችን አገነዛዘብ ‼️
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
|| የቴሌግራም ቻናል :- 👇
https://t.me/Mistre_ahbashe
https://t.me/Mistre_ahbashe





