ጥቅምት 13/2018 ዓ/ም(ኢኢግ)ለኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና መ/ቤት ሴት ሰራተኞች የጡት ካንሰር እና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ ግንዛቤ ማስጨበጫ እና ምርመራ ተሰጠ፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አገልግሎት ሀላፊ ሐና ታምራት (ሲ/ር) ወሩ ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም ሴቶች ቅድመ መከላከልን እንደ ልምድ ሊወስዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫው አላማ የሴቶች ጤና አጠባበቅ ስርዓትንን ለማዘመንና ዘመናዊ አኗኗርን ለመከተል ያግዛል፡፡ የተገኘውን ግንዛቤ ከራሳችን ባሻገር ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
መርሃ ግብሩ የግሩፑ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አገልግሎት ከአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጋር በመተባበር ከለቡ ጤና ጣቢያ በመጡ ባለሙያዎች እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
October 23, 2025 2.3K 3







