ላ አንስታ ለበሰች፡፡ ሙሉ ለሙሉ ራቁቷን ነበረች፡፡ አንሶላውን ተጋራት፡፡ ዝም እንዳሉ መሸ፡፡ አስር የለ፣ መግሪብ የለ ፣ ኢሻ የለ ….. ዝም! ሁለቱም ልብ ውስጥ በዚህ ሁኔታ ፈጣሪ ፊት የመቆም ድፍረት የለም፡፡ ዝምታው ሲደክማት ተጠግታ ተለጠፈችበት፡፡ አቀፋት፡፡
‹‹ኢምሩዬ አፈቅርሀለሁ እሺ!››
‹‹እኔም እወድሻለሁ!››
‹‹የምርህን ነው?››
‹‹ይመስለኛል! ባልወድሽ ይህን ያህል አልቀርብሽም ነበር፡፡››
ፊቷ ላይ የደስታ ብርሀን በራ፡፡ እንዳታልፈው እስኪሰጋ ድረስ ተለጠፈችበት፡፡ የወደደችውን ስላገኘች ….. ህይወቷን ልትሰጠው የምትፈልገው ሰው ስለተቀበላት ….. ደስ ብሏታል፡፡
‹‹ግን ቀሙ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ አይደል?››
‹‹የቱ?››
‹‹አሁን ካንቺ ጋር መተኛቴ!››
‹‹በጣም ይቅርታ ኢምሩዬ! አማራጭ የነበረኝ አልመሰለኝም!››
ቀና ብላ ከንፈሩን ሳመችው፡፡ መፀፀት የጀመረው ያገኘው እርካታ አልቆበት ከሆነ ብላ ማደንዘዣዋን ደገመችው ….. ሳመችው፡፡ በጣም ደካማ ነበር፡፡ ስትስመው ተመልሶ ስሜቱ ውስጥ ሰጠመ፡፡ የፍራሿ ስቃይ ቀጠለ፡፡ እሱም ሆነ እሷ በፍፁም ራሳቸውን በዚህ አይነት ወራዳ ተግባር ውስጥ እናገኛለን ብለው አስበው አያውቁም፡፡ ጭንቅላቷን ተጠቅማ እያሸነፈች ነበር፡፡ አሁን ግን በአቋራጭ ለማሸነፍ ብላ ሴትነቷን ተጠቀመች፡፡ ሴት ልጅ መሸነፍ የምትጀምረው ሴትነቷን መጠቀም ስትጀምር ነው፡፡ ዛሬ ኢምራን ተደፈረ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መድፈር በጉልበት ማነቅ ብቻ አይደለም፡፡ እንዲህ በውበት ሀይል …. እንዲህ በስሜት ሀይል አስገድዶ እጅ እንዲሰጥ ማድረግም መድፈር ነው፡፡
ጠዋቱን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ሁለት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ ቀመር የወር አበባ ላይ ሆና ሰላት የማትሰግድባቸው ቀናትን እንኳ ልምድ ሆኖባት በንጋት ስግደት ሰዓት ትባንን ነበር፡፡ ኢምራንም የሷው ቢጤ ነው፡፡ ወንጀል ፤ ሰሪውን ከመልካም ስራ እንደምትከለክል ለመረዳት የሻ ሰው ሁለቱን መመልከት ይበቃዋል፡፡ የትናንትናው ወንጀላቸው ከስግደት ሲከለክላቸው … ደነገጡ፡፡
‹‹ሁለት ሰዓት ሆኖ ነው?›› ቀመር ሰውነቷን በአንሶላው እንደጠቀለለች ስልኳን ፈልጋ ስትመለከት ማመን ከብዷት የጠየቀችው ነበር፡፡
‹‹ማለት ነዋ እንግዲህ! ምነው ደነገጥሽ?››
‹‹ፈጅር ሳንሰግድ ብዬ ነዋ!›› ፈጅር ጎህ ሲቀድ የሚሰገደው የንጋት ስግደት መሆኑ ነው፡፡
‹‹ትናንት አስር ፣ መግሪብ እና ኢሻም አልሰገድንም ከረሳሽው ላስታውስሽ!››
ቅስሟ ስብር እንዳለ ወደ ፍራሹ ተመለሰች፡፡ ገና ለስግደት ብቁ ለመሆን ጀናባ ማውረድ የሚባለው መስፈርት ይቀራቸዋል፡፡ ገላቸውን መታጠብ አለባቸው፡፡ ያኔ ጀናባቸው ወረደ ይባላል፡፡ ኢምራን ከወ/ሮ አርሴ መዘፍዘፊያ ተውሶ ቀመር ቤቱ ውስጥ ገላዋን እንድትታጠብ እሱ ደግሞ ግቢው ውስጥ እንደነገሩ በቆርቆሮ የታጠረችው ክፍል ውሀ ይዞ ሄዶ ለመታጠብ አሰበ፡፡ ቱታውን ለብሶ ወደ ወ/ሮ አርሴ ቤት ሲሄድ ወ/ሮ አርሴ እና ሌሎች ተከራዮች ቤቱ ውስጥ ሲሰራ የነበረውን ወንጀል ያወቁ ፣ ያወቁ እየመሰለው ያፍር ነበር …. እነሱ ግድ ይሰጣቸው ይመስል ይጠራጠራቸዋል! የሚመለከተው ….. ከመመልከት ምንም የማይጋርደው ጌታው ግን ያልተፈቀደለትን ቀለበት በማህተሙ ሲዘጋ እየተመለከተው ነበር፡፡ እሱ ያውቃል …. እሱ ተወንጅሏል ….. ግን ምንም አላለም! አይቸኩልማ!
.
ይቀጥላል …
@Lib_Weled
December 6, 2021 8.6K 22