Legal Case የህግ ጉዳይ: post #160 — TG.ME

18.  ግልፅ ሕግ የለወጠ የሰበር ትርጉም። በቤተሰብ ህጉ ድንጋጌ ከባልና ሚስት ያለ አንደኛዉ ተጋቢ ፈቃድ  ወይም ስምምነት የተደረገ ዉል እንዲፈርስ የሚቀርብ ዳኝነት ጥያቄ ዉሉ መደረጉ ከታወቀበት ቀን  ጀምሮ በስድስት ወር ጊዜ ዉስጥ ሆኖ በማንኛዉም ሁኔታ ዉሉ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በሁለት  ዓመት ጊዜ ዉስጥ መቅረብ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ይሁንና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር  ሰሚ  ከባልና ሚስት አንደኛዉ ተጋቢ ያለ  ሌላኛዉ ተጋቢ ፈቃድ ወይም ስምምነት የተደረገ የስጦታ ዉል እንዲፈርስ የሚቀርብ የዳኝነት  ጥያቄን አስመልክቶ ተፈፃሚነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ የስጦታ ዉልን ልዩ ባህሪ መሠረት ያደረገ  ሊሆን ይገባል የሚል ምክንያት በመስጠት፣ ተፈፃሚነት ያለዉ በቤተሰብ ህጉ ላይ የተመለከተዉ  ሳይሆን በፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 1845 ላይ የተመለከተዉ የአስር ዓመት የይርጋ ጊዜ ሊሆን  እንደሚገባ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። የሰ/መ/ቁ=247605 ጥቅምት 05/2017 19.  እርቅ በገደብ ለመለቀቅ መስፈርት ነው(የሰበር መዝገብ ቁጥር - 266395 ቀን - 26/06/2017 ዓ.ም) ስለ ገደብ ጥያቄ በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 185700 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ከግል ተበዳይ ጋር ታርቆ ካሳ መክፈል በወንጀል ህጉ አንቀፅ 197 መሰረት ጥፋተኛው በተሰጠው የፈተና ጊዜ ውስጥ በመልካም ጠባይ እንዲመራ እና በፈተና ጊዜ ውስጥ ተገቢውን ፍሬ እንዲያፈራ በሚል ለመልካም ጠባይ አመራር ዋስትና የሚሰጥ ትዕዛዝ እንጂ ቅጣትን ለመገደብ ቅድመ ሁኔታዎች እንዳልሆኑ ትርጉም ሰጥቷል ፡፡ በወ/ህ አንቀፅ 192 ስር ቅጣቱን ለመገደብ ያልተቀመጡ ምክንያቶችን በመዘርዘር ከግል ተበዳይ ጋር ታርቆ ገንዘቡን አልከፈለም የሚል ምክንያት በማስቀመጥ እና ከተጠሪ በኩል ስለ እርቅ ጉዳይ ክርክር ሳይቀርብ በራሱ አነሳሽነት ያልተጠየቀ ዳኝነት በመስጠት ቅጣቱ ሊገደብ አይገባም በማለት መወሰኑ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 185700 ላይ ከሰጠው የህግ ትርጉም ጋር የሚጣረስ ውሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል፡፡ 20.   የገንዘብ መጠንና የቅጣት ክብደት ጉዳይ "ከባድ እምነት ማጉደል" የጉዳዩ ጭብጥ: የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31(2) ላይ ያለው "የደረሰው ጉዳት ከፍተኛነት" የሚለው መቼ ነው ለከባድ ቅጣት የሚያበቃው? የሰበር ችሎቱ ብይን: የገንዘብ መጠኑን (ለምሳሌ ከብር 100,000 በላይ) ብቻ ሳይሆን፣ ድርጊቱ በተፈጸመበት ወቅት ያለውን የብር የመግዛት አቅም፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ሁኔታ እና የሕጉን ዓላማ መሠረት አድርጎ መወሰን ያስፈልጋል።በዚህ ጉዳይ ላይ ብር 203,022.81 ድርጊቱ በተፈጸመበት ወቅት የነበረው የመግዛት አቅም ሲታይ ለከፍተኛ ቅጣት የሚያበቃ "ከፍተኛ ጉዳት" አይደለም! የቀድሞው የ 7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት ቅጣት ተሻሽሎ ወደ 3 ዓመት ፅኑ እስራት ወርዷል! ለሕግ ተማሪዎችና ለጠበቆች እጅግ ጠቃሚ የሕግ መርህ! የሰበር መ/ቁጥር: 25857 ዓ/ም/ ቀን: ጥር 29 ቀን 2017 21.  ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ መዝገብ ቁጥር 242314 ከዚህ ቀደም ያለተቃውሞ ወይም በፈቃድ በሌላ ሰው መሬት ላይ ሕንጻ የሰራ ሰው በመሬቱ ላይ መብት እንደሚያገኝ በማረጋገጥ የተሰጡ ውሳኔዎች በሙሉ በሰበር መዝገብ ቁጥር 242314 ተለውጠዋል፡፡   በሌላ ሰው የመሬት ይዞታ ላይ ግንባታ ያካሄደ ሰው በሕንጻው ላይ ሊኖረው የሚችለው መብት በፍ/ህ/ቁ. 1178 እና 1179 ድንጋጌዎች በተመለከተው አግባብ የሚታይ ሲሆን ሕንጻ በመገንባቱ ብቻ በመሬት ይዞታዉ ላይ መብት የሚያሥገኘዉ አይደለም በሚል ተተርጉሟል፡፡ ጠበቃ Yonas Woldeyes ዮናስ ወልደየስ 🙏🙏🙏

January 1, 2026 1K 18