Legal Case የህግ ጉዳይ: post #159 — TG.ME

15.  የፌደራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ/ቁ. 251383 በቀን. 07-02-2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር ላይ የተሰጠ ውሳኔ ሲሆን አስቀድሞ በንብረት ላይ ውሳኔ ከተሰጠና ንብረትም ተከፋፍሎ ከተጠናቀቀ በኋላ አደስ ንብረት ቢገኝ የተገኘው ንብረት ይከፈልልኝ በሚል የሚቀርብ ክስና የሚጠየቅ ዳኝነት በድጋሚ የቀረበ ክስ ነው ሊባል የማይገባ መሆኑን በሚመለከት የተሰጠ ውሳኔ ነው 16.  በዳግም ዳኝነት አስቀድሞ የተሰጠን ውሳኔ መሻር(የሰ/መ/ቁ 250597 ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 112258 ፤ 115377 እና በሌሎችም መዛግብት በሰጠው ውሳኔ የሚመለከተው የአስተዳደር አካል በሰጠው ምላሽ መነሻነት የተሰጠን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ  6 ላይ በተቀመጡት ሁኔታዎች ተገቢ ያልሆነ ማስረጃ ቀርቦ የተሰጠ ውሳኔ መኖሩ ካልተረጋገጠ በቀር በዳግም ዳኝነት አስቀድሞ የተሰጠን ውሳኔ መሻር እንደማይቻል በመግለጽ አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም የሰጠ ሲሆን በሌላ በኩል አንድ የመንግስት አካል እውነተኛውን ሳይጣራ መሰጠት የማይገባውን ሀሰተኛ ማስረጃ ለፍርድ ቤት በመስጠቱ ውሳኔ የተሰጠበት ወገን ማስረጃው ሀሰተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እስካቀረበ ድረስ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 6/1/ መስፈርትን አያሟላም ሊባል እንደማይገባና አቤቱታ አቅራቢው ሀሰተኛ መረጃ የተሰጠው በመንግስት አካል መሆኑን ከማስረዳት አልፎ የመንግስት አካል ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር የፈፀመበትን ምክንያት ማስረዳት እንደማይጠበቅበት ጭምር በሰ/መ/ቁ 91968 ( ቅጽ 15 የታተመ ) ላይ ገዢ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል፡፡ 17.  ክሱን አመልካቾች እንዲያሻሽሉ ከፈቀደ በኋላ ተገቢ አይደለም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 208 መሰረት በማረም ክሱ ሊሻሻል አይገባም የማለቱን አግባብነት ከስነ ስርዓቱ ህጉ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ትዕዛዝ በበላይ ፍ/ቤት ከሚሻር በቀር በድጋሚ ትእዛዙን በሰጠው ፍ/ቤት እንደ አጻጻፍ ስህተት ተቆጥሮ በራሱ በፍ/ቤቱ ትዕዛዙ መነሳቱ የስነስርዓት ህጉን የተከተለ አይደለም የሰ/መ/ቁ 246954 ጥቅምት 8 ቀን 2017 የፌ/ጠ/ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሰ/መ/ቁ. 138445 ከገጠር መሬት ጋር ተያይዘው የሚነሱ አለመግባባቶችና ክርክሮች በስምምነትና በሽምግልና መፈታት ካልቻሉ ክልሎች በሚያወጡት ህግ መሠረት ውሳኔ እንዲያገኙ በአዋጅ ቁጥር 456/97 መደንገጉንና የተከራካሪ ወገኖች መደበኛ መኖሪያ ቦታ ከግምት ሳይገባ ከእርሻ መሬት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ክርክሮች ካላቸው ልዩ ባህሪ አንጻር በክልል ህግ ሥልጣን በሚሰጣቸው ፍርድ ቤቶች ብቻ እንዲፈቱ በመወሰኑ ከገጠር የእርሻ መሬት ይዞታ ጋር ተያይዘው ክርክሮች በመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን የማየት ስልጣን ያለው የገጠር እርሻ ይዞታው የሚገኝበት የመሬት የዳኝነት ኮሚቴ በመሆኑ ጉዳዩን የፌዴራል ጉዳይ አያደርገውም በማለት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ የስር ፍ/ቤት ክሱን እንዲያሻሽሉ ከፈቀደ በኋላ ተገቢ አይደለም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 208 መሰረት በማረም ክሱ ሊሻሻል አይገባም የማለቱን አግባብነት ከስነስርዓቱ ህጉ አኳያ ክርክሩ በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ብይን የመስጠቱን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ያስቀርባል በማለት የስር ፍ/ቤት የሰጠው ትዕዛዝ በበላይ ፍ/ቤት ከሚሻር በቀር ድጋሚ ትእዛዙን በሰጠው ፍ/ቤት እንደ አጻጻፍ ስህተት ተቆጥሮ በራሱ በፍ/ቤቱ ትዕዛዙ መነሳቱ የስነስርዓት ህጉን የተከተለ አይደለም ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል(0910214108)

January 1, 2026 761 13