Legal Case የህግ ጉዳይ: post #158 — TG.ME

12.  ኤርትራዉያን (መ/ቁ 247259 ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ.ም) በመንግስት መመሪያ ከሃገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩ ኤርትራዊያንን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ከወጡ ጀምሮ ተፈቅዶላቸው እስከተመለሱ ድረስ ያለው ጊዜ በይርጋው ውስጥ ሊታሰብ የሚችልበት የህግ አግባብ እንደማይኖር ይህ ሰበር ችሎት የፍ/ብ/ህ/ቁ.1845 እና 1846 ድንጋጌዎችን በመተርጎም በሰበር መዝገብ ቁጥር 92408፣ 98177፣ 158255 እና በሌሎችም መዛግብት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠ ሲሆን ይኸው ትርጉም በህጉ አግባብ እስካልተለወጠ ድረስ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 መሰረት በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረው ነው፡፡ መ/ቁ 247259 ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ.ም 13.በወ/መ/ሥ/ህ/ቁ 67/ሐ/መሰረት ተከሳሽ በዋስትና ቢወጣ ማስረጃ ሊያጠፋና ምስክር ሊያባብል ይችላል በሚል ዋስትና ሊነፈግ የሚችለው ምስክሮቹ ገና ለፖሊስ ቃላቸዉን ያልሰጡ ሲሆን እንጂ ምርመራ ተጠናቆ መደበኛ ክስ ከተመሰረተ በኋላ አይደለም። በዚህ ምክንያት ዋስትናን መከልከል ከፍርድ በፊት እንደ ንጹህ የመቆጠር ህገመንግስታዊ መብት የሚጥስ ነው የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትሰ/መ/ቁ =273144/ታህሳስ 21 ቀን 2017 14.  የሰበር ውሳኔ ወደኃላ ተመልሶ ይሰራል ወይ ✅የወራሽነት የምስክር ወረቀት ስለያዝን በማንኛውም ጊዜ(ያለ ይርጋ ገደብ) የውርስ ንብረት ጥያቄ ማንሳት እንችላልን በማለት የውርስ ሀብቱ ሳያጣሩ የቀደመ ሰበር አቋምና የህግ ትርጉም አምነው የተቀመጡ ሰዎች ያላቸው መፍትሄ ምንድ ነው ? ሰ/መ/ቁ.243973 ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ውሳኔ ከተሰጠበት በኃላ ውርስ የተከፈተ ከሆነ አከራካሪ አይደለም። ✅ሰበር ሰሚ ችሎቱ በሰመቁ 255592 በቀን ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ያለኝ እይታ። በዚህ መዝገብ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋጠዉ አውራሾች ጥር 25 ቀን 2003 ዓም እና ጥር 04 ቀን 2004 ዓም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ወራሾች በ29/08/2005 ዓም ወራሽነታቸውን አረጋግጠው ውርሱ ሳይጣራ መኖሪያ ቤቱን ሳይከፋፈል ቆይቶ በ2015 ዓ.ም ክፍፍል መጠየቃቸውን ነው። ✅ሰበር ሰሚ ችሎቱ  ለውሳኔው መሰረት ያደረገው በሰ/መ/ቁ.243973 ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በሰባት ዳኞች “ የወራሽነት የምስክር ወረቀት የያዘ ሰው በማንኛውም ጊዜ(ያለ ይርጋ ገደብ) የውርስ ንብረት ጥያቄ ማንሳት ይችላል በሚል ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁ. 205248 /መ/ቁ. 44237፣38533 ወዘተ) የተሰጡ የህግ ትርጉም በመለወጥ 1) የውርስ ማጣራት ተጠናቆ ንብረቱ የጋራ ባልሆነበት ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት በመያዝ ብቻ የፍ/ሕ/ቁ. 1062 መሰረት በማድረግ ያለጊዜ ገደብ የክፍፍል ጥያቄ ሊነሳ እንደማይችል 2) የወራሽነት ማስረጃ መያዝ አለመያዝ ልዩነት ሳይኖረው  በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የወራሽነት ጥያቄ ካልቀረበ ክሱ በይርጋ ይታገዳል በማለት ውሳኔ የሰጠበትን መሰረት በማድረግ ነው። ✅ሰበር ሰሚ ችሎቱ በሰመቁ 255592 ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በሰ/መ/ቁ.243973 ጥቅምት 06 ቀን 2017 የተሰጠው ውሳኔ መሰረት በመሆኑ ሰመቁ 243973 የተሰጠው የህግ ትርጉም ወደ ኃላ ተመልሶ ስራ ላይ እንዲውል ያደረገ ነው ። ✅እርግጥ ነው የሰበር ውሳኔ የህግ ትርጉም እንጂ የህግ አይደለም ሕግ የማውጣት ስልጣን አልተሰጠውም የሚለውን ክርክር እንደተጠበቀ ሆኖ በፅንሰ ሀሰብ ትክክል ቢሆንም በተግባርና በውጤት ግን ሕግ ነው‌። ✅የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በማናቸውም ደረጃ ባሉት የፌዴራልም ሆነ የክልል ፍርድ ቤቶች ላይ የአስገዳጅነት ኃይል ያለው ስለመሆኑ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች  አዋጅ ቁጥር 1234 አንቀፅ 10(2) ደንግጓል። ከዚህ ድንጋጌ ያለው በስተጀርባ ያለው መሰረታዊ የህግ መርህ (principle of non retroactivity of laws) ህግ ወደ ኃላ ተመልሶ አይሰራም የሚለውን ነው። የዚህ መርህ መነሻ ሀሳብ የህግ ትርጉም የሚሰጠው የህብረተሰብ ማህበራዊ ግንኙነት ለማሳለጥ እና ለመቆጣጠር እንደመሆኑ መጠን የህግ ትርጉሙ ተፈፃሚነት የሚኖረው ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የተፈጠረ እና ለወደፊት የሚፈጠውን ግንኙነት ላይ እንጂ ውሳኔ ከመውጣቱ በፊት የተፈጠረውን ኩነት ብቻ በመሆኑ። ✅ለውርስ ክርክር ተፈጻሚነት ያለው ሟች በሞተበት እና ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ በስራ ላይ በነበረው ህግ እንጂ ክርክሩ በቀረበ ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት አለመሆኑ፤ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥሮች 86089፣ 99587፣ 121822 እና 183645 ላይ ለውርስ ክርክር ተፈጻሚነት ያለው ሟች በሞተበት እና ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ የነበረው ህግ ሳይሆን ክርክሩ በቀረበ ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት ሊሆን ይገባል በማለት የሰጠው ትርጉም ተለውጧል በማለት በሰባት ዳኞች በሰመቁ 191393 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።

January 1, 2026 585 13