Legal Case የህግ ጉዳይ: post #157 — TG.ME

Forwarded fromአለአለ ሕግ

11.  ሥረ-ነገሩ ተመሳሳይ ሆኖ ነገር ግን የሚያዘው ወይም የተያዘው ጭብጥ የተለያየ ከሆነ በተያዘው ጭብጥ ላይ የቀድመ ፍርድ ባለመኖሩ ጉዳዩ በፍርድ እንዳለቀ ሳይቆጠር ክርክሩ ቀጥሎ ፍርድ ሊያርፍበት የሚችል ጉዳይ ነው፡፡      የተከራካሪዎች ተመሳሳይነት የሚለው ከተከራካሪዎች በሕግ ሆነ በውል መብት የተላለፈላቸውን ሦስተኛ ወገኖች የመብታቸው ምንጭ የቀድሞው ክርክር ላይ ተከራካሪ በሆኑት ወገኖች ልክ በመሆኑ በእነዚህ ወገኖች ላይም ጉዳዩ አስቀድሞ በፍርድ እንዳለቀ የሚያስቆጥር ነው፡የሰ/መ/ቁጥር 246803 ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ/ም  ክርክሮች በአነስተኛ ወጪና ምክንያታዊ በሆነ አጭር ጊዜ ፍትሐዊ እልባት የሚያገኙበትን የክርክር ሂደት አመራር ስርዓት መዘርጋትን መሰረታዊ ኢላማው ያደረገው የፍትሐ ብሀር ስነስርዓት ህጋችን ተከራካሪ ወገኖች ለአላስፈሊጊ የጊዜና የወጪ ብክነት ሳይዳረጉ ክርክሮች በአንድ ደረጃ መቋጫ እንዲያገኙ የሚያደርግ (finality) ሥነ ሥርዓት መዘርጋት እንዲችል ፤ የፍርድ ቤቶች የክርክር አመራር በአነስተኛና ምክንያታዊ በሆነ የጊዜ፣የሰዉ እና የገንዘብ ሀብት አጠቃቀም (judicial economy) ተከናዉኖ ወጥነት ያለውን (consistent) እልባት እንዲያገኝ ጥብቅ ክትትልን እንዲተገብሩ፤ እንዲሁም ተከራካሪዎች አስቀድሞ ዉሳኔ ባገኘ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ክስ በማቅረብ የፍትሐ ብሔር ፍትህ አመራር ሒደቱን ባልተገባ መንገድ እንዳይጠቀሙና ተከሳሾችን ባልተገባ ሁኔታ እንዳያጉላላ ጥበቃን ማድረግ እንዲያስችሊቸው በአንቀፅ 5(1) ላይ በሕግ ሥልጣን የተሠጠው ማናቸውም ፍርድ ቤት ክርክሩን ተቀብሎ የመጨረሻ ፍርድ ከሠጠ በዋላ ቀድሞ በፍርድ የተወሰነው ክርክር ሥረ-ነገርና የተያዘው ጭብጥ አንድ ዓይነት ከሆነ በክርክሩ ላይ የነበሩት ወይም ከተከራካሪዎቹ መብት ያገኙ ሦስተኛ ወገኖች በዚያው ነገር ሁለተኛ ክስ ለማቅረብ የማይችል መሆኑን ደንግጓል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት ጉዳዩ አስቀድሞ በፍርድ አልቋል ለማለት በድንጋጌው በዝርዝር የተመለከቱት አራት መስፈርቶች በአንድነት መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡👇 1)የመጀመሪያው መስፈርት ጉዳዩን በመጀመሪያ ከተመለከተው ፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣን ጋር የተያያዘ ሲሆን በአንቀፅ 5(1) በሕግ ሥልጣን የተሠጠው ማናቸውም ፍርድ ቤት በማለት የተመለከተው የህግ ሀረግ አስቀድሞ ጉዳዩ የታየው በሕግ ዳኝነት ለመስጠት ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ወይም ዳኝነት ነክ አካል መሆኑን ማረጋገጥን የሚጠይቅ የህጉ መሰረታዊ መስፈርት መሆኑን ከድንጋጌው አጠቃላይ ይዘት የምንረዳው ነው። 2)ሁለተኛው መስፈርት አስቀድሞ በፍርድ ቤት የተሠጠው የመጨረሻ ፍርድ ነው በሚል ከዚያ በኋላ የቀረበውን ክስ ውድቅ ለማድረግ የተመለከተው መስፈርት ፍርድ ቤቱ ክርክሩን አይቶ ጉዳዩ ሊይ የመጨረሻ እልባት ወይም ውጤት የሠጠበት መሆን እንዳለበት የሚያስረዳ መስፈርት ሲሆን 3)ሦስተኛው መስፈርት አስቀድሞ ፍርድ ያረፈበት ጉዳይ ሥረ-ነገሩና ጭብጡ አሁን ከተያዘው ጉዳይ ጋር አንድ ዓይነት መሆን እንዳለበት የሚያመለክተው ነው። 4)አራተኛው መስፈርት የተከራካሪዎች ወይም ከተከራካሪዎች መብት ያገኙ ሦስተኛ ወገኖች ተመሳሳይ መሆን እና በእነርሱ መካከል ያለ ክርክር መሆኑ ነው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5፣ 244(2/ለ) እና 245/2 የተመለከተውንና እነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ይህ ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁጥር 28522፣ 36780፤243645- እና በላልች መዛግብት ሊይ የሰጣቸዉን አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች ይመለከቷል)፡፡

❤1
January 1, 2026 421 11