Legal Case የህግ ጉዳይ: post #156 — TG.ME

Forwarded fromአለአለ ሕግ

8. የዉል አካል የሆኑ ሰነዶች በተዋዋዮች መካከል ባለዉ ዉል ልክ የጸና ነዉ(ሰበር መ/ቁ=241479=ጥቅምት 5/2017) በመሠረቱ የሥር ፍርድ ቤት በፍርዱ ሀተታ ላይ በግራ ቀኙ መሐከል ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ/ምአመልካቹ የኤክስሬይ ማሽን ለማቅረብ፣ ተጠሪው ደግሞ ለመግዛት ውል መፈጸማቸውን ከዚህጋርም አጠቃላይ የውሉ ሁኔታዎች፣ ልዩ የውል ሁኔታዎች፣ የፍላጎት መግለጫ፣ የጨረታመስከበሪያ ወረቀትና አቅራቢው ያቀረባቸው የዋጋ ዝርዝሮች፣ ግዢ ፈጻሚው አካል ለአቅራቢውጨረታ ማሸነፉን ያሳወቀበት ሰነድ እና አቅራቢው ለመወዳደሪያ ያቀረበው የተያያዘ መስፈርትናሌሎች ሰነዶችም የውሉ አካል መሆናቸውን ውል ያደረጉበት ሰነድ የሚያስረዳ ስለመሆኑ የገለጸሲሆን፣ አቅራቢ የሆነው አመልካቹ ለመወዳደሪያ ያቀረበው መስፈርትን የሥር ፍርድ ቤቱ የውሉ አካል መሆኑን አረጋግጦ እያለ፤ ይህንን የአመልካቹን የመወዳደሪያ ሰነድ በውሳኔው ላይ ግምትሳይሰጥ አልፎታል፡፡ ይህ የውሉ አካል የተደረገ በውላቸው አንቀጽ 2/ረ ላይ የተመለከተው አቅራቢ የሆነው አመልካቹ ያቀረበው የመወዳደሪያ የተያያዘ መስፈርት የውሉ አካል በመሆኑና የተጠሪው ዋና መከራከሪያ የኤክስሬይ ማሽኑን አመላካቹ ማቅረብ የነበረበት፣ ተጠሪ ጨረታውን ባወጣበት የፍላጎት ዝርዝር መግለጫ መሠረት መሆን ነበረበት ከሚል በቀር፤ የኤክስሬይ ማሽኑ በአመልካቹ ባቀረበውና የጨረታው አሸናፊ በሆነበት መስፈርት መሠረት አልቀረበም የሚል መከራከሪያ በተጠሪ በኩል ያልቀረበ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ወየውሉ አካል በተደረገው አመልካቹ ባቀረበው የመወዳደሪያ ሰነድ መሠረት የኤክስሬይ ማሽኑን ያቀረበ ሆነ እያለ የአመልካቹን የመወዳደሪያ ሰነድ እንደ ውሉ አካል ሳይቆጥር በማለፍ ተጠሪው ጨረታ ያወጣበትን የተጠሪውን የፍላጎት መግለጫ ብቻ መሰረት በማድረግ አመልካቹ ያቀረበው ማሽን በውላቸው ከተመለከተው ውጪ በመሆኑ በውሉ ላይ የተመለከተውን ገንዘብ ተጠሪው ሊከፍል አይገባም የሚለው የሥር ፍርድ ቤቱ ድምዳሜ እራሱ ያረጋገጠውን አቅራቢው ለመወዳደሪያ ያቀረበው የተያያዘ መስፈርትና ሌሎች ሰነዶችም የውሉ አካል መሆናቸውን ከግምት ያላስገባ በመሆኑ አመልካቹ ለተጠሪ አቅርቦ እንዳስረከበውን የተረጋገጠውን የኤክስሬይ ማሽን ዋጋ ተጠሪው የመክፈል ግዴታ የለበትም በማለት አመልካች ማሽኑ በራሱ ወጪ አንስቶ እንዲወስድ በማለት የሰጠው ውሳኔ የማስረጃ ምዘና ጉድለትያለበት በመሆኑ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመት ሲሆን፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይህን ጉድለት ሳያርም በመቅረት የአመልካቹን የይግባኝ ቅሬታ መሰረዙ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው 9. የፌዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 163896 የክልል የመሬት ሕግ በግልጽ በሟች የሚደረግ ኑዛዜ አካለ መጠን ያልደረሰን የሟችን ልጅ ከዉርስ መንቀል እንደማይችል የደነገገ ቢሆንም አካለ መጠን የደረሰዉን የሟች ልጅ በተመለከተ በፍትብሔር ሕጉ ድንጋጌዎች መሠረት ተፈጻሚ እንደሚሆነ በመግለጽ አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል ፤ የፍትብሔር ሕጉ ደግሞ ወደታች የሚቆጠርን ልጅ በዝምታ ከዉርስ መንቀል እንደማይቻል ይደነግጋል፤የሰመ.ቁጥር 251074 ጥቅምት 07 ቀን 2017 ዓ/ም 10. የገጠር መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር/የባለቤትነት ሰነድ የሚያሰጠው የባለቤትነት መብት ግምት እና ሊስተባበል የሚቻልበት ህጋዊ አግባብነት )ሰበር መዝገብ ቁጥር 244423 በ24/03/2017 የተሰጠ ውሳኔ)፡- በመርህ ደረጃ የከተማም ሆነ የገጠር የይዞታ ባለቤትነት የሚረጋገጠው ስልጣን ባላው የመሬት አስተዳደር ተረጋግጠው የተሰጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ (title deed) በመቅረብ እንደሆነ ከፍ/ብ/ሕ ቁጥር 1206 እና 1195 መገንዘብ ይቻላል። ሆኖም ግን የይዞታ ባለቤትነት ምዝገባ ያልተካሄደባቸው አከባቢዎች በመኖራቸው እና በተለያዩ ሌላ ምክንያቶች የባለቤትነት ሰነድ ላይኖር የምችልባቸው ሰፊ አጋጣሚዎች ስላሉ የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ከtitle deed ውጭ በሌላ ማስረጃ ማስረዳት አይቻልም ማለት እንዳልሆነ ልብ ልባል ይገባል። እንደዝሁም ምንም ህጋዊ መብት ሳይኖር በሌላ ሰው ሰነድ ኣልባ ይዞታ ላይ በህገወጥ መንገድ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የምሰጥበት ሁኔታም እንዳለ የገሃዱ ዐለም እውነታ ነው። በተጨማርም በህግ ፍት ተቀባይነት የሌላቸው ወይም ፈራሽ የሆኑ የመሬት ሽያጭ ወይም ክራይ ውሎችን መሠረት በመድረግ የምሰጥ የባለቤትነት ማረጋገጫ እንዳለም የተለመደ ነው።እንግድህ ከላይ በተነገሩትም ሆነ በሌላ ማንኛውም መንገደ የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ/ማስረጃ የተሰጠው ሰው የይዞታው ህጋዊ ባለቤት እንደሆነ የህግ ግምት የምያስወስድ መሆኑ በፍ/ብ/ህጉ አንቀፅ 1195 በግልፅ ተደንግጒል። ክርክር በተነሳ ግዜ ማስረጃው የተሰጠበት መንገድ ህግን የተከተለ አለመሆኑን ወይም በህግ የተከለከለ ወይም ፈራሽ በሆነ ውል ላይ ተመስርተው የተሰጠ መሆኑን በየትኛውም አይነት ማስረጃ በማስረዳት በፍ/ብ/ህጉ ቁጥር 1196 መሠረት በህጉ ቁጥር 1195 የተወሰዳውን ግምት ማፍረስ ወይም ማስተባበል ይቻላል።እንግድህ ከላይ በተጠቀሰው የሰበር መዝገብ ቁጥር የፌዴራሉ ሰበር ፍ/ቤት ውሳኔ የሰጠበት ጉዳይ ስዳማ ክልል በአርቤጎና የመጀመሪያ ደረጃ የቀረበና በየደረጃው ባሉት የክልሉ ፍ/ቤቶች በይግባኝ እና በክልሉ በመታያት ፌዴራል ሰበር የደረሰ ነው።የጉዳዩ ፍሬ ነገር በአጭሩ ስገለፅ በክልሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፌዴራሉ ሰበር ተጠሪ የሆነቹ ባለቤቷ የሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ እና 2ኛ ተከሳሽ በሆነው የፌዴራሉ ሰበር አመልካች ላይ ባቀረበችው ክስ የባልና ምስት የጋራ የሆነን ለክሷ ምክንያት የሆነውን የገጠር መሬት ያለሷ እውቅናና ፈቃድ 1ኛ ተከሳሽ ለ2ኛ ተከሳሽ የሸጠ መሆኑን በመዘርዘር ገልፃ ውሉ ፈርሶ አመልካች መሬቱን አእንድለቅ እንድወሰንላት ዳኝነት ጠይቃለች። ባሏ የሆነው 1ኛ ተከሳሽ በወቅቱ ገዝብ ቸግሮት ከላከሳሿ ፈቃድ መሬቱን ለአመልካች መሸጡን በመግለፅ ክሱን ኣምነው መልስ የሰጠ ስሆን የፌዴራል ሰበር አመልካች ወይም የክልሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 2ኛ ተከሳሽ በበኩሉ መሬቱ የግሉ ይዞታ መሆኑን፣ ለዝሁም ከምመለከተው የመሬት አስተዳደር ይዞታ ማረጋገጫ ተሰጥተውት ቋሚ ንብረት አፍርተውበት ከ14 አመት በላይ እየኖረበት ያለው የግሉ ይዞታ እንጅ ከከሳሽ ባለቤት ጋር ያደረገ ምንም አይነት ውል አለመኖሩን በመዘርዘር መልስ ሰጥተው የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተሩን በማስረጃነት አያይዘው ተከራክሯል። የክልሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሳሽ መሬቱ የራሷና የባለቤቷ የጋራ ሀብት እንደሆነ እና በህገወጥ ውል በ2ኛ ተከሳሽ መያዙን በሷ ከመግለፅ ውጭ የተባለው ውል መደረጉን የምያሳይም ሆነ መሬቱ በ2ኛ ተከሳሽ የሷ ወይም የባሏ ወይም የጋራቸው የነበረ መሆኑን የምያሳይ ነዉ፡፡

❤2
January 1, 2026 411 13