Legal Case የህግ ጉዳይ: post #154 — TG.ME

#በ2017 ዓ.ም #የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት #ሰበር ሰሚ #ችሎት #ምርጥ 21 ዉሳኔዎ‼️ 1. የስጦታ ውሉ በተዘዋዋሪ የመሬት ሽያጭ ውጤት ያለው ከሆነ ተቀባይነት የለውም ፡-ተጠሪዎች ከመሠረቱት ሕገ ወጥ በሆነ ስጦታ ውል አማካኝነት መብት አቋቁሜያለሁ በሚል የአመልካቾችን አውራሽ በሐይል እና በጉልበት የያዙት ይዞታ ለቀው እንድያስረክቡ በሚል ያቀረቡት የዳኝነት ጥያቄ የውልን መፍረስ ዳኝነት ጥያቄ የሚጠበቅ ሳይሆን ፍ/ቤቱ በራሱ በሕገወጥ መንገድ የተገኘ የመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የመጣ ክርክር በመሆኑ የስጦታ ውሉ በተዘዋዋሪ የመሬት ሽያጭ ውጤት በሚያስከትል መልኩ ስምምነት የተደረገበት በመሆኑ በሕግ ዘንድ ተቀባይነት የለውም በማለት ክርክሩን ውድቅ ማድረግ ሲገባው የስጦታ ውሉን እውቅና በመስጠት እና ተጠሪዎች በዚሕ ሕጋዊ ባልሆነ የውል ግንኙነት አማካኝነት በይዞታው ላይ ለረጂም ጊዜ ግብር መገበራቼው የይዞታው ባለመብት ያደርጋቸዋል በማለት አመልካቾች ክርክር ያስነሳውን ይዞታ ለቀው ለተጠሪዎች ያስረክቡ በሚል የተሰጠው ውሳኔ ከሕግ አተገባበር እና ማስረጃ ምዘና አንጻር መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ስለመሆኑ ተወስኗል (መ/ቁ=257723 ታሕሳስ 25/2017))

January 1, 2026 512 13