ገቢዎች ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጉምሩክ ዋጋ አተማመን መመሪያ ቁጥር 1080/2017 አውጥቷል፡፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው እና በጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ተፈርሞ ለሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተላከው ደብዳቤ የዋጋ አተማመን መመሪያው ከህዳር 5/2018 ዓም ጀምሮ በስራ ላይ መዋሉን ያስረዳል። አዲሱ መመሪያ :- • ወደ ሀገር በሚገባ እና በሚወጣ ማንኛውም ዕቃ፣ • ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ከጉምሩክ ቁጥጥር የተለቀቀ ዕቃ ወይም የተሟላ የጉምሩክ ስነስርዓት ያልተፈፀመበት ዕቃ ሆኖ ቀረጥና ታክስ ለማስከፈል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ • የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ተፈጽሞበት በተለቀቀ ዕቃ ላይ የድህረ ዕቃ አወጣጥ ኦዲት ሲከናወን፣ • ንግድ ላልሆነ ዓላማ ወደ ሀገር በሚገባ ወይም/እና በጊዜያዊነት ወደ ሀገር የሚገባ ዕቃ ዋጋ አተማመን ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲሱ መመሪያ በሁሉም የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ በስራ ላይ የዋለ መሆኑን ከጉምሩክ ኮሚሽን አረጋግጧል። ባለ 47 ገጽ ዝርዝር መመሪያውን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ። @tikvahethiopia
1
1November 18, 2025 1.4K 1