Forwarded fromየሕግ ቤት
እንድታውቁት! ላላወቁትም እንድታጋሩት!!! ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገልጋዮች በሙሉ የፍትሐብሄር ይግባኝ ችሎት የስራ ቦታ ለውጥ ** የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሄር ይግባኝ ችሎት አራት ኪሎ ባለው የኢትዮ-ፓስታ ህንፃ ላይ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከጥቅምት 3 ቀን (ሰኞ) 2018 ዓ.ም ጀምሮ የፍትሐብሄር ይግባኝ ችሎቱ አራት ኪሎ ከአብረሆት ላይብረሪ ወደ ፒያሳ መሄጃ 100 ሜትር ወረድ ብሎ ፍርድ ቤቱ እያስገነባ ወደሚገኘው አዲሱ ህንፃ ተዛውሮ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን እየገለፅን ከላይ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የይግባኝ ችሎቱ ተገልጋዮች አገልግሎት ማግኘት የሚችሉት በአዲሱ ህንፃ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በአማራጭ የጎግል ማፕ (google map) ሊንክ 2QH6+VC7, Addis Ababa በመጠቀም አቅጣጫውን ማግኘት ይችላሉ። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
1October 9, 2025 816 1