ሩፋኤል አሳድገኝ ልጅ እያለን ልክ ጷጉሜ 3 ዝናብ ሲዘንብ አሳድገኝ አሳድገኝ እያልን ዝናቡ ውስጥ እንሮጥ… — ኩራዝ — TG.ME

ሩፋኤል አሳድገኝ ልጅ እያለን ልክ ጷጉሜ 3 ዝናብ ሲዘንብ አሳድገኝ አሳድገኝ እያልን ዝናቡ ውስጥ እንሮጥ ነበር አሁን ላይ ግን ሳስበው በእድሜ በተክለ ሰውነት አድገን ግን በመንፈሳዊነት ቀንጭረናል ትላንት በልጅነታችን ቂም አንይዝም አሁን ግን የበደሉንን ካልተበቀልን ክብራችን የወረደ ይመስለናል ብቻ በብዙ ነገር ቀንጭረናል አሜን ሩፋኤል ያሳድገን አሁን ቀንጭረናልና በልጅነታችን በዝናቡ (ፀበል)ስንጠመቅ ሰውነታችንን ቆሽሾ ሊሆን ይችላል ልባችን ግን እንደ ወርቅ ንፁ ነበር አሁን ግን መዓዛችን ያማረ ሆኖ ነፍሳችን ከርፍቻለች በሀጢያት እድፍ ሩፋኤል ሆይ የነፍሴን እድፍ እንዳፀዳ ምልጃህ ይደግፈኝ ለማንኛውም ስለ ዛሬዋ ቀን ትንሽ ልበላቹ በዚች ዕለት ሰማያት ይከፈታሉ የክርስቲያኖችም ፀሎት ቅዱስ ሩፋኤል ያሳርጋል የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባት አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ አላቸው። ጦቢ 12:15 ምን ይሄ ብቻ ይሄ ድንቅ ምልአክ በቁስል ላይም የተሾመ ስለሆነ በፀበሉ በፍፁም ካመንን ካለብን ደዌም በሽታ ሁሉ እንነፃለን እንድናለን ሁለተኛውም በበሽታው ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመ ቅዱስ ሩፋኤል ነው አለኝ።ሄኖ 10:13 ጌታ በስራችን ተቆጥቶን ካላስቀረብን በዛሬው ዕለት የሚዘንበው ዝንባ እንደ ከዚህ ቀደሙ ዝናብ ብቻ አይደለም የቅዱስ ሩፋኤል ፀበል እንጂ በዚህ ቀን ሰብሉ ይባረካል በሰብል ላይ ያሉና ሰብል የሚበሉ ነፍሳት ይጠፋሉ ይሄ ደሞ በአይንም እያየንው ያለ እውነታ ነው በዚህ ቀን የሚዘንበው ፀበል ተቀድቶ ይቀመጣል እህል ይቦካበታል እንዲበረክት እቤት ይረጫል አጋንንት እንዲያርቅ ቅዱስ ሩፋኤል ሰዳዲ ሴጣን ነውና(ሴጣንን አሳዳጅ) ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ አግዘው አለው። _ሄኖ 3:5 እንጠመቅበታለን ከደዌ ከበሽታ እንድንርቅ ግን ስንቀዳው ቀጥታ የሚወርድ መሆን አለበት ማለትም በመንጮሮር ከሆነ ቆሻሻ ሊቀላቀል ስለሚችል ከጥታ ከሰማይ የሚወርደውን መቅዳት ይመከራል(ግዴታ ባይሆንም) ብቻ ምን አለፋቹ ይቺ ቀን የተለየችና የተባረከች ዕለት ናት መልአክ ፀበሉን ባርኮ ከደዌ እንደሚያነፃ ማስረጃ ምትፈልጉ ፕሮቴስታቶች ይሄው ተመልከቱ “አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።” — ዮሐንስ 5፥4 መልካም በዓል ለወዳጅዎ ያጋሩ ቻናሉን ይቀላቀሉ ✍✍Esuye ከሀጢያተኞች ዋና 1ኛ ጢሞ 1:15

September 8, 2026 173