እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለቅዱስ ሩፋኤል አመታዊ በዓል! ቅዱስ ሩፋኤል ሩፋኤል ማለት ፈውስ ማለት ሲሆን… — ኩራዝ — TG.ME

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለቅዱስ ሩፋኤል አመታዊ በዓል! ቅዱስ ሩፋኤል ሩፋኤል ማለት ፈውስ ማለት ሲሆን ይኸውም በአምላክ ለሰው ልጆች ፈውስ ፣ መድኃኒት ፣ ዐቃቤ ሥራይ ፣ መንፈሳዊ ሀኪም ማለት ነው ። ስሙ ግብሩንና ሹመቱን በሚገባ የሚገልጥ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሦስተኛ ሲሆን በራማ ኹለተኛ ክፍል ያሉት የመናብርት አለቃ ነው ። ቅዱስ ሩፋኤል በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዙትን ሊ ፈውስ በመናፍስት ላይ የተሾመ ነውና የሰው ልጅ በእርኩሳን መናፍስት እጅ ሲወድቅና ለሞት ሲጋለጥ ፈጥኖ የሚላክ መልአክ ነው ። ቅዱስ ሩፋኤል የገባኤል ልጅ የኾነውን ጦቢትንም ለማዳን የተላከ ነው። ጦቢት በአሦር ንጉሥ በስልምናሶር ከተቢስ ተማርከው ወየ ነነዌ ከወረዱት ዐስሩ ነገድ መካከል ሲሆን በዚህም በሙሴ ሕግ ጸንቶ ፣ በጾም፣ በጸሎትና በምጽዋት በመትጋት በበጎ ሥራ ይኖር ነበር ። ይኸ ሰውን በመርዳት ደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ በዚያው ሌልት ከቅጥሩ አጠገብ ተኛ። ፊቱን ገልጦ ነበርና በአዕዋፍ ፋንድያ ምክንያት አይኑ ጠፍቶ ባለ መድኃኒት ሁሉ አላድነው ብሎ ከቤት ቀረ። ያን ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል እርሱንና እንደ ሳምራዊቷ ሴት ባሎቿ ጭኗ ላይ በሞት ይሰናበቷት የነበረችውን የራጉኤልን ልጅ ሳራንም ለማዳን ተልኮ በመምጣት ቁራኛ ጋኔን አስወጥቶ የጦቢት ልጅ ጦቢያ እንዲያገባት አድርጓል። በዚኸም " ፈታሔ ማህፀን " ተብሏል። በኋላም ወደ ጦቢት በመሄድ አይኑን አብርቶለት " ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነኝ " ብሏቸው ተሰውሯል። ይህንን ገቢረ ተአምራቱን በማየት ምእመናን የወላድ ማህፀን እንዲፈታ ስለ ተሾመ አዋላጅ ብትኖር ባትኖርም ሐኪም ሩፋኤል አይታጣም ብለው በምጥ ጊዜ ሲጨነቁ መልአኩን መልክ በአንገታቸው አስረው ፣ ማየ ጸሎቱን ጠጥተው ቶሎ ፈጥነው ይወልዳሉ። ያዘኑትን በማረጋጋቱ መስተፈስሔ አልባብ ናዛዜ ሕዙናን ተብሏል። ከባለ እንጀሮቹ ጋር ለሰው ልጆች ምህረትን የሚለምን በጳጉሜ ፫ ቀን የተሾመ መዛግብተ ሰማይን የሚከክትና የሚዘጋ እንዲሁም በደብረ ጽዮን ለምሳ የተጠሩትን የግብጽ ፣ የቆሰሉትን ሁሉ የሚፈውስ ታላቅ መለአክ ነው ። ስለዚህም ነገር " ኸለተኛውን በበሽታ ኹሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመ ቅዱስ ሩፋኤል ነው አለኝ።" ሄኖ ፲፥፲፫ ይላል ነብዩ ሔኖክ። በየወሩ በዐሥራ ሦስት ቀን የሚታሰብ ሲሆን ይኸውም ከእስክንድርያ ውጪ በደሴት የታነጸች ቤተ ክርስቲያኑ ቅዳሴ ቤት የተከበረበት ነው ። ዓመታዊ በአሉም መታሰቢያ ጳጉሜ ፫ ቀን ሲሆን በዚህ ቀን ጸሎታችን ሁሉ የሚሰማበትና ዝናቡ ሳይቀር ጸበል ሁኖልን እኩያን አጋንንት ከእኛ የሚርቅበት ነው ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር

September 7, 2026 140 3