አዲስ ቀን መጣ 🌼 የአዲስ ዘመንን እልፍ በረከት ይኸው አገኘን በአንተ ቸርነት በጨለማው ላይ ቀን የምታወጣ… — ኩራዝ — TG.ME

🌼 አዲስ ቀን መጣ 🌼

የአዲስ ዘመንን እልፍ በረከት
ይኸው አገኘን በአንተ ቸርነት
በጨለማው ላይ ቀን የምታወጣ
ስምህ ከፍ ይበል አዲስ ቀን መጣ

የዜማ ጊዜ ደርሶ ስላየን
እኛስ ለስሙ እልፍ ቅኔ አለን
ምድርን ቀድሷት አበባው ፈካ
ፍጥረት ዘመረ ሰፍቶ እንደ ዋርካ
ተሰጠን ዘመን አዲስ ዕለት
ለአሳየን ቀንን አዲስ ዓመት
ተመስገን በሉ ያዙ በገና
ቅኔ እስከ አርያም ይገባልና

አዝ= = =
መጸው ፀደዩን ተቀደስንበት
በጋ ክረምቱን አወደስንበት
ዘመን ሲቀየር እንድንለወጥ
አለን ፈጣሪ ከእሳት የሚመርጥ
ተሰጠን ዘመን አዲስ ዕለት
ለአሳየን ቀንን አዲስ ዓመት
ተመስገን በሉ ያዙ በገና
ቅኔ እስከ አርያም ይገባልና

አዝ= = =
ቀስተ ደመናው ጉም አስከትሎ
ታየ በሰማይ መወድስ አዝሎ
የምድሪቱ ገጽ ለአንተ ቃል አለው
የአዝናማት ጌታ ቀን የምትቀይረው
ተሰጠን ዘመን አዲስ ዕለት
ለአሳየን ቀንን አዲስ ዓመት
ተመስገን በሉ ያዙ በገና
ቅኔ እስከ አርያም ይገባልና

አዝ= = =
ጉድለት እንዲሸሽ ያ ጉስቁልና
ቸር እንዲያሰማን በጎና ደህና
እንዘምራለን በብዙ ትጋት
ለአንተ ውለታ ለአንተ ቸርነት
ተሰጠን ዘመን አዲስ ዕለት
ለአሳየን ቀንን አዲስ ዓመት
ተመስገን በሉ ያዙ በገና
ቅኔ እስከ አርያም ይገባልና


መዝሙር
አዜብ ከበደ

🌼🌼🌼
https://t.me/maedot_ze_orthodox
♡ አዲስ ቀን መጣ ♡
September 5, 2026 92 3