✨KB Orthodox✝️: post #7654 — TG.ME

እንኳን ከዘመነ ጸደይ ወደ ዘመነ ክረምት መሸጋገሪያ ለሆነችው ዕለት ሰኔ 25 በሰላም አደረሳችሁ !

ቅድስት ቤተ ክርስቲያ] ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በአራት ዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች ። እሊሕም ዘመናት መጸው [ጽጌ] ፣ ዘመነ ሐጋይ [በጋ] ፣ ዘመነ ጸደይ [በልግ] እና ዘመነ ክረምት ናቸው ። ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ከማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል ።

በተለይ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ሽሽታችሁ [ስደታችሁ] በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" ብሎናልና [ማቴ.፳፬፥፳] (24:20) አብዝተን ልንጸልይ ይገባናል ። በዘመነ ክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ የለበትምና ፍሬ ምግባር ሣናፈራ ሞት እንዳይመጣ ፤ አንድም ክረምት የዝናብና የጭቃ ጊዜ በመሆኑ እንኩዋንስ ለስደት ለኑሮም አይመችም ። አበው ስለ ዝናም ሲያስተምሩ ዝናም ወደ መሬት ሲወርድ አንድ ጊዜ ዠቅ ብሎ በሙላ አለመውረዱ መከራ በመጠን በአቅም ለመሰጠቱ ምሳሌ ነው ይሉናል ። ከሰኔ 25 - መስከረም 25 በሚቆየው ወርኃ ክረምት በልዩነት የመከራ ወቅት ምሳሌ ነውና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጸልይ :-

"በዝንቱ ፡ ክረምት ፡ በመዋዕሊነ ፡ እንበለ ፡ ፍሬ ፡ እንዘ ፡ በቆጽል ፡ ኀሎነ ፡ ናስተበቁዐከ ፡ እግዚኦ ፡ ኢይኩን ፡ ጉያነ ።"... #ትርጉም [ ክረምት ፡ በተባለ ፡ በእኛ እድሜ ፡ ፍሬ ፡ ሳናፈራ ፡ በቅጠል ፡ /ያለ ፡ መልካም ፡ ሥራ/ ፡ ሳለን : አቤቱ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስደትን ፡ አታምጣብን ፡፡ ]

ስለ ዝናም ጸልዩ !


@KB_ORTHODOX
😘4❤2🥰1🙏1😍1
July 2, 2026 164