✨KB Orthodox✝️: post #7652 — TG.ME

የማኅበራዊ ሚዲያ ፈተና

በአሁን ሰዓት የአዳም ዘር መብሉ ፣ መጠጡ ፣ ወሬውም ሆነ ሁለመናው ማኅበራዊ ሚዲያ እየሆነ መጥቷል። ፌስቡክ ፣ ኢንስተግራም ፣ ዩቱብ ፣ ቲክቶክ በቀላሉ ስለሚከፈቱ ከትንሽ እስከ ትልቁ ከፍቶ ይዝናናል ። ሰው ፎቶውን ፣ የበላውን የጠጣውን ፣ ያየውን ፣ የሰማውን ይለጥፋል ፣ ይሰድባል ፣ ያመሰግናል ፣ ይረግማል ይመርቃል። ከሁሉም መተግበሪያዎች ጀርባ ግን ምን እንዳለ የሚያውቁ ጥቂቶች ብቻ ይመስሉኛል። 

ማኅበራዊ ሚዲያ በአግባቡ ካልተያወ በነገው ትውልድ ላይ ትልቅ ሱስ የሚሆን እየሆነም ያለ ይመስለኛል ። የሰው ልጆችን አኗኗር በእጅጉ ይቀይራል ፣ ጤንነት ይቃወሳል ፣ አንገትና ጀርባ በልጅነት ይጎብጣል ፣ አይን ያለጊዜው ይደብዝዛል ፣ ነገ ላይ ቀጥ ብሎ መሄድ ተረስቶ ዛሬ "የእጅ መታጠብ ቀን" እንደ ሚባለው " ከቲክቶክ ነጻ ቀን" ተብሎ ቢከበር ደስ ይለኛል ። 

ሰው ከሰው ጋር ንግግር ቀንሶ ከግዑዝ ነገር ጋር ያወራል ማሰብ ማሰላሰል ያቆማል። የሰው የመመራመር አቅም በእጅጉ ይጎዳል። እውቀቱ ተሰብስቦና ተሸብቦ ከኢንተርኔት ብቻ ይሆናል መጽሐፍ ማገላበጥ ጌጥ ይሆናል። በጊዜው ወላጅ ራሱንና ልጁን ያርም ይዘጋጅ ካልሆነ ጣጣው ቀላል አይሆንም ለዛሬ አንድ ነገር ብቻ ልጠቁም። ቲክቶክም ሆነ ፌስቡክ የራሳቸው የሚሰሩበት ስልት (algorithm) አላቸው። ሰዎችን በጾታ ፣ በሀገር ፣ በእድሜ በመሳሰሉት ነገር ይከፍሏቸዋል።

ለምሳሌ ቲክቶክ ባለቤቱ ቻይና ውስጥ ያለ ነው ይባላል ። ስለሆነም ታላላቅ የወጣት ስኬት ፣ የፈጠራ ክህሎት ፣ ስፓርታዊ ውድድር ፣ አስገራሚ የሳይንስ ግኝት ፣ የሒሳብ ውድድር ፣ ሥራ ፈጣሪነት ፣ ወጣቶች ለራሳቸው ስኬት ሲሰሩ የሚያሳይ ሲለጠፍ ቲክቶክ ወደ ከፈቱ የቻይና ወጣቶች ይሄዳል። 

እንድንደቅ (እንድንደነዘዝ) የምንፈለገው እኛ ደግሞ ጦርነት ፣ ግድያ ፣ ሥራ አጥነት ፣ የራቁት ዳንስ ፣ ሴትና ወንድ በአጸያፊ መልኩ ሲገናኙ ፣ ስድብ ፣ ሎተሪ ቆርጦ ስለወጣለት ሰው ፣ ፕራንክ ሲደራረጉ ፣ ሰዎች መጠጥ ቤት ተቀምጠው ፣ ባል ሚስትን ሲያታልል….. እንደ ጉድ ወደ እኛ ይከማቻል ይፈሳል ። አንድም የምናየው ተከታታይ ቪዲዮ የእኛን ማንነት እስከ ማሳወቅ ይደርሳል ። በዚህ የመጣ አይናችን እና ጭንቅላታችን  ዞሮ እንተኛለን።

ይህ አይነት ነገር ደጋግሞ የሚመጣብህ ከሆነ መጫወቻና ቁሻሻ መጣያ ሆነሃል ። ኒውክለር ሳይተኮስ አንተን መግደል ማለት ይሄ ነው ። አንተ የምታየውን ዝባዝንኬ የቻይና ወጣት አያይም ። የቻይና አሊጎሪዝምና የአሜሪካ አሊጎሪዝም ይለያያል ለአፍሪካ ደግሞ አስበው ። ስለሆነም ሰፊ ማሰላሰል ይፈልጋል ። ስልክ እያየን ስንሄድ ፣ ስንነዳ የምንጋጭ ብዙ ነን ።  ይህችን ለጥቆማ የጻፍኳት ናት ፈተናው ግን ቀላል አይሆንም እናስብበት ለማለት ነው።
👍5❤2😘2🥰1😍1
May 16, 2026 331 1