*<<በልቤ በር ቆመህ እያንኳኳህ የምትጠብቀኝ እኔ ማነኝ ?*
ጌታ ሆይ የሚያስቆይ አመል ኖሮኝ ነው የጠበከኝ ? ምኔን አይተህ ነው የታገስከኝ ?
የፈጠርከኝ እኔ ፣ ሁሉ ነገሬ ያንተ ሲሆን ሁሉን መስጠት ሲገባኝ ትንሿን ትኩረቴን ነሳሁህ ! የሰጠኸኝን ጉልበት ላንተ ማድረግ አቃተኝ ! የሰጠኸኝን ጊዜ እኔ ግን ትንሿን ለአንተ ማካፈል አልቻልኩም !
ታድያ ለምን ? የእውነት ለምን ብለህ እስካሁን ከደጄ ቆመሀል ?
መሄጃ ሳይኖርህ እኮ አይደለም ከልቤ የቆምከው አንተ እኮ ታላቅ ነህ ታድያ እኔ ስር ምን ትሰራለህ ?
*ፍቅር !*
አዎ ከእኔ ጋር ከፍቅር ውጪ ምን አለህ ? ምግባር የለኝ ፣ እምነት የለኝ ፣ አንተን የሚፈልግ ልብ የለኝ ...
ጌታ ሆይ እስክከፍትልህ አትጠብቅ በተዘጋ በር የገባህ አንተ በተቆለፈውም ልቤ ሳታስፈቅደኝ ግባ !
እኔ ለ እኔ መሆን አልቻልኩምና እኔነቴን ገዝተህ የአንተ አድርገኝ !
5
2
1
1May 13, 2026 307 2