ውበቱ ባይማርክ የፊቱ ገፅታ፣
ምንም ከመልኩ ላይ ባይገባም ከእይታ፣
ግና ኑር ነበረ ኑርን የወደደ፣
የልቡ ላይ ሁቡ ነቢይን የሰነደ።
ምንም ደሀ ቢሆን ባይኖረው ቆጠሮ፣
ምንም በአይን ቢታይ ከቁመቱ አጥሮ፣
የዚያ ዘመን ሰዎች
ዘር ግንዱን እያዩ
አድልተው ለውበት፣
አገለሉት አሉ ክብር እንደመስጠት።
ጁለይቢይ መች አጣ የሚወደው ከቶ፣
ከአላህም ከረሱል ውዴታ ተሰቶ፣
ጁለይቢይ ከእኔ ነው
እኔም ከእሱ ነኝ፣
ብለው አወደሱት መልከ መልካሙ አዛኝ።
ጥሪት ከቆጠሮ
ባይኖረው ከጓዳ፣
ከመልኩ ቢደብስ
ቁመቱ ባይፀዳ፣
ለትዳር ፍለጋ
ባይወጣም ከሜዳ፣
ግና ነቢይ ዳሩት
መልካሟን ኮረዳ።
ስሙ ባይታወቅ በዙሪያው ነዋሪ፣
ዘነጋው ከቦታው የእገሌው ተጣሪ፣
ጁለይቢይን አጣሁት ፈልጉልኝ እማ፣
ብለው አወደሱት የአለሙ ራህማ።
ባለ 7 ታሪክ ክንደ ብርቱው ያ ሰው፣
ከጀሀድ ሜዳ ላይ ሂዶ የወደቀው፣
7 ወዲያ ጥሎ ዲኑን ሲል የሞተው፣
በነብዩ እጅ ነው ለህድ የተንተራሰው።
#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
#የኸሚስ_ብዕሮች

4August 13, 2026 286