#ለኸሚሳችን 52
.
.
.
...........አንቱን ስል
እንኳን ሰው መሆንን
ግመል አስከብሮል፣
የአንቱ መሆን ነቢይ
ስንቱን ሰው ሞሽሮል።
ካልቀበሩኝ በቀር እሩህ ከእኔ ሸሽቶ፣
ካልዛለ በስተቀር ይህ ክንዴ ተረቶ፣
ካልከፈኑኝ በጨርቅ አይኔ ካልተዘጋ፣
ስላንቱ እከትባለሁ በቆላም በደጋ።
እኔ ምን ቸገረኝ
አንቱን ስል ቢጠሉኝ፣
ስድባቸው ምርቃን
ጥፊያቸው አይጎዳኝ።
አንቱን ስል ቢጠሉኝ
አንቱን ስል ነብዬ፣
ግድ የለኝም ጭራሽ
ቢያገሉኝ ውድዬ።
እንኳን ጥየሁ ልሄድ ጓዞቼን ጠቅልዬ፣
እንኳንስ ልራመድ አንቱን ወዲያ ብዬ፣
ማሰብ ያሳመኛል በልቤ ማስታወስ፣
ታቅፌሁ እኖራለሁ እስከ ለህዴ ድረስ።
አንቱን ስል ቢጠላኝ
አንቱል ስል ቢጋፋ፣
አንቱን ስል የራቀኝ
ከጎኔ ቢጠፋ፣
ግድ የለኝም እና አንቱን ስል ለሄደ፣
መታኮሱን ትቶ ይምጣ እየበረደ።
ባያውቅሁ ነው እንጂ ያወቀሁ መች ሄዶ፣
አንቱን ሲል ይኖራል ቀለም ፊደል ሰዶ፣
የግንባርሁን ኑር መቶ ያየው ለታ፣
ሊሰድብሁ የመጣው ቀረ በዝምታ።
አንቱን ስል ልሙተው
ሳልጠፋ ከደጅሁ፣
ልመላለስበት
ከሚያበራው ከስምሁ፣
አድሮ ከሚንረው
ወዝቶ እየፈለቀ፣
ከስምሁ ልዋልል
አይኔ እየሰበቀ።
ወገግ ከሚለው ከስምሁ ዳርቻ፣
ኑርን ከሚያስንቀው ከመልክሁ መባቻ፣
መዝለቁ ቢገደን ቁመን ከዳር ዳሩ፣
መፃፉን ይዘናል እያልን ሙክታሩ።
አንቱን ስል ከጠላኝ ከኢማኑ ጎሎ፣
አንቱን ስል ይውደደኝ ጥሉን ወዲያ ጥሎ፣
ከስሮ ከሚከስር ጎሎ እየጎደለ፣
ወዳጅሁን ይውደድ መውደድ እያከለ።
ከምሎ በካሚል መጉደል እየራቀው፣
ማነሱ እየበዛ አንዳችም ሳይከላው፣
ሰለዋቱ በአንቱ በዘመድ الصحابة፣
አበደን ቀን ለይሉን ይውረድ እየረባ።
ተፃፈ-በፈትሁዲን ዑመር
ሙሀረም-1448 ዐ.ሂ /ሰኔ-2018 ዐ.ል
.
.
.
#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
10June 18, 2026 700