ኢንፋቅ የልማትና መረዳጃ ማህበር /ደሴ/: post #39230 — TG.ME

ኢንፋቅ የልማትና መረዳጃ ማህበር /ደሴ/#ለኸሚሳችን . ልዩ የስነ-ፅሁፍ ምሽት በኢንፋቅ ልማትና መረዳጃ ማህበር የቴሌግራም ቻናል ይከታተላሉን! . በየሳምንቱ ኸሚስ ምሽት . #ኢንፋቅ_ሚዲያ #ኢንፋቅ
#ለኸሚሳችን 51
.
.
.
..............አፍሬ ነው

ተው ጀሰዴ ተው እባክህ
አታክስረኝ መንገድ ለቀህ።

ተይኝ ነፍሴ ተይ አድቢ፣
መልስ የለሽም ከስራሽ ዘንድ ስትቀርቢ።

ምናለበት
ባትረክሺ ባታረክሽኝ፣
ቀና እንዳልኩኝ
ይህ አንገቴን ባታስደፊኝ።

ተይኝ ነፍሴ አትራመጅ ወደ ዞላም፣
ተወዳጅቶ ከክፉ ዘንድ ቀኝ አይሰላም፣
የሄደ ሰው በአባሙራ በሱ መንገድ፣
ሆኖል ትርፉ በፀፀት ደጅ በእሳት መንደድ።

አፍሬ ነው እንጂ መዲና ማልመኝ፣
እንጂ መች ጠላሁት ከወዳአንቱ ብገኝ፣
ከወዳአንቱ ቀዬ ከአረንጓዴው ቁባ፣
መገኘት መች ጠላሁ ሆንኩ እንጂ ማረባ።

አፍሬ ነው እንጂ
በምግባሬ ማነስ በውድቅ ማንነቴ፣
እንጂማ መች ጠላ አንቱን ሰውነቴ።

የሚያሳዝን ቢሆን የርምጃዬ ነገር፣
ቢያድፍ ሰውነቴ በአጉል ስደናገር፣
ማነሴ እያነሰ ከጭላጭ ስር ብናኝ፣
ማፈሬ በረታ ከአንቱ እርቄ ብገኝ።

አፍሬ ነው ሆዴ
አንቱ የኔ መውደድ፣
ስራዬ ከስራሁ
እርቆ ቢንጋደድ፤

አስቀረኝ መሰለኝ
የራሴው ስንክሳር፣
ላፍታ መጣ ብዬ
ወዳአንቱ እንዳልሀድር።

አፍሬ ነው አፍሬ ነው ቀና ማልል፣
አቀርቅሬ የቀረሁት ብጎዳድል፣
ብሞላማ የአንቱን ሱና ብራመደው፣
ባልተከዘ ሰውነቴም ባላፈረው።

አንተ ሀጁ ተሳፋሪው ተመዲና፣
የሰራሁት ያረከሰኝ
ያመፅኩበት ያሳነሰኝ
ያደፍኩበት ዝቅ ያረገኝ
እስኪሸሸኝ፤
ይህ አንገቴ እስኪቃና እስኪያነሳኝ፣
ለወዳጄ ሰላምታዬን አድርስልኝ።

ሶሊ ወሰሊሙ ዳኢመን በጠና፣
ተኩለው በመጡት በኑሮቹ ዋና፣
በቤተሰብ ጓዶዎ ሰርክ በምልልስ፣
ሰለዋቱ ይንጎድ ሁለዜም እንደ አዲስ።

ተፃፈ-በፈትሁዲን ዑመር
1447 ዐ.ሂ

.
.
.
#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
❤7
June 11, 2026 634 2