.
.
.
--------------መሰናበቻው
በመሰናበቻው በንግግራቸው፣
አላውቅም እያሉ ለሚመጣው አመት ለመገኘታቸው፣
የለም የሚመጣ መልዕክተኛ ሆላ፣
ህዝብም የለም የሚፈጠር ከዚህ ሌላ።
በመሰናበቻው በሀጁ ስንብት፣
በሀጀተል ወዳዕ በሚንበሩ መልዕክት፣
እናንተ ሰዎች ሆይ ብለዋል በአደራ፣
ስለ ሰው ልጅ ክብር በነቢይ ተወራ።
ደግሞም ከልክለዋል አራጣን በጠና፣
ስለ ሴቶች መብት አስፍረው በዋና፣
ተናግረው በቃላት ስለ ዲኑ መምላት፣
በእኩልነት ሰብከው ኑሩ አሉ በአንድነት።
መስክሩልኝ ብለው ስለ መልዕክት መድረስ
ለሶሀበታቸው፣
ቢሉ ያንን ጊዜ ሶሀባው በቃላት መሰከሩላቸው፣
ከዚያም የአላሁ መስክርልኝ ብለው፣
ቆጩ ምክራቸውን ሊሄዱ ጠቅልለው።
መቼም ያማል ይሄ ወጉ ላደመጠው፣
እንኳን በአካል በነበረው በሀደረው፣
በሌለው ሰው በዚያ ዘመን ባልተገኘው፣
ከአይኑ አፍስሶል ይኸ ኸበር የደረሰው።
መዲናይቱ በቀን ፀሀይ ስትጨልም፣
ሀዘን ወርሷት ዞላም ከቧት ስትል እልም፣
ሶሀበቶች ክው ሲሉ ውስጥ ነዶ፣
ሰይፍ ሳቡ ያ ኡመር ማመን ገዶ።
የሄዱ እለት የመዲናው የኑር አምባ፣
ሞላት ሀዘን ሂጃዚቱን እያደባ፣
ቀምቶ አዛን ቅላፄውን ውቡን ቃና፣
አባረረው ያንን ቢላል ከመዲና።
በአንቱ መምጣት
የተዋበው ያ ጎዳና፣
የሄዱ እለት
ሀዘን ቃኘው እንደገና፣
የአንቱ መምጣት
ከፍ ያረጋት መዲናይቱ፣
የሄዱ እለት
ከብዷት ታዬ መፅናናቱ።
ወዳጄዋ ምኞቴ ነው የጧት ማታ፣
መጎራበት ከአንቱ ቅጥር በዚያ ቦታ፣
የሞትኩ እለት ሲዘጋጋ ሙላው ሁላ፣
ወዳጅ ሁኑኝ አማላጄ ለእኔው መላ።
ሶሊ ወሰሊሙ ዳኢመን አበዳ፣
በዚያ መልከ ውቡ በእኔው ሙሀመዳ፣
ይርከፍከፍ ዘላለም ይውረድ ያለ ፋታ፣
ይዋልልም ይዝነብ ያላንዳች ጋብታ።
ተፃፈ-በፈትሁዲን ኡመር
1447ዐ.ሂ_2018ዐ.ል
.
.
.
#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
