ኢንፋቅ የልማትና መረዳጃ ማህበር /ደሴ/: post #39228 — TG.ME

#ለኸሚሳችን 49
.
.
.
.............-የምን ቅድስና
.

በውልደቴ ምድር በእኔ እትብት መርጊያ፣
ወዴት ልሂድ ጥዬ ምነው አጣህ ማያ።

ቅድስት ናት አልከኝ
አንተው አርክሰሀት
በመጠጥ አረንቆ
በአረቂ ገላሀት።
ቅድስት ነሽ አልካት?

የምን ቅድስና
አንተው አርክለሀት ስሟን ጥለህ ሜዳ፣
ደሞ ትጋፋለህ እሷ ሙስሊም ወልዳ።

በገዛ ሀገሬ ወዴት ልሂድ እኔ፣
ሞቼም የሄድኩ ቀን ወዴት ይረፍ ጎኔ፣
ምነው ለከት አጣ የጭካኔህ ወሰን፣
ቆሻሻ አስመሰልከኝ ቀብረህ እንደማዘን።

የምን ቅድስና
ለበድን ገላዬ አፈር ሆነህ ከልካይ፣
ቅድስት ነኝ ብትል አትሆንም የበላይ።

ትውልድ ይወቅሰሀል በተራ በተራ፣
ዛሬ ወዲህ ሆነህ ለሰራሀው ስራ፣
ለሰራኸው በደል ለግፍህ አረንቋ፣
ነገ ይጠፋሀል መናገሪያ ቋንቋ።

ዩሀንስ በዳግም በዘመን ሊደገም፣
ሲቃጣ እያዬሁት የማይሆን ሊቀለም፣
ለትውልድ ሊሻገር በብራና ሰፍሮ፣
ይኸው ተጎስሞል የበደል ከበሮ።

አይበጅም ተመለስ
ባለ ቅድስት ወጉ፣
ሙስሊም ጡሀራ ነው
የስር ማዕረጉ።

የምን ቅድስና
ነጃሳ ታቅፎ፣
ራስ ማታለል ነው
መጠጥ ተደግፎ።

ይልቅ መቻቻልን ተክለህ ለትውልዱ፣
የመስጅዱ ቅያስ ተሰምሮ መንገዱ፣
ካስማው ተንሰራፍቶ ምሶሶው ተቃንቶ፣
አዛኑ ይሰማ ከህዋው ላይ ጎልቶ።

አክሱም የጋራ ነች ልክ እንደ ሰመራ፣
አብላጫ እንኳ ቢሆን የእምነቱ ጎራ፣
መቻቻል ነው እንጂ የሚበጀው ለሰው፣
መቻል ለቅፅበት ነው ኖሪ እስከሚመረው።

የምን ቅድስና
ሽፍንፍኑን ገላ ይገለጥ እያሉ፣
እረክሰው ሊያረክሷት ወዲያ እያገለሉ።
ቅድስት ነኝ አሉ!?

አዛን ሳይሰማ መስጅድ ሳይሰራ፣
የመቃብር ቦታው ካሬው ሳይመራ፣
የሂጃቧ መብት በውል ሳይጣራ፣
ቅድስት ነኝ ማለት ሁኖል ለእኔ ተራ።
.
.
ተፃፈ-በፈትሁዲን ዑመር
1447ዐ.ሂ

.
.
.
#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
❤4
May 28, 2026 711