.
.
.
'''''''''''''''''''''''''''''-ሳይሰዬም
መብረር መሄድ ልብ አያርፍም፣
መዲና ስር ሳይሰየም።
ሳይሰየም ከአጥሩ ቅጥር አረፍ ብሎ፣
እንዴት ይርጋ የወዳጅ ልብ አዘንብሎ።
ተጀሰዱ ባይገኝም ባህር ማዶ፣
የእግር ኮቴው ባይራመድ መዳፍ ሰዶ፣
አረፍ ባይል ከአንቱ አውራጃ ተቀምጦ፣
መናቡ ግን ሁሌ እዛ ነው አንቱን መርጦ።
ሀቢበሏህ የአላህ ወዳጅ
የእኔ አማላጅ፣
ከቶ ምነው እንዲህ መራቅ
እስከምፈጅ።
ምነው መቅረት ለጠባቂ
ማርፈድዎ፣
ታዩት እንጂ ከስቶ አለቀ
አንቱን ብሎዎ።
አጉድዬ አማናዎን ስጠለፍ በወንጀል፣
ትላንት ደህና ሆኜ ዛሬ ደግሞ ስቀል፣
ስወድቅ ስነሳ ተው ባሉኝ ስራመድ፣
ሀፍረት ብቻ ሆነ መገን የኔስ መንገድ።
ትቼዎት አልሄድም
በእርግጥ አንቱን ጥዬ፣
በውድቀቴ ማግስት
እላለሁ ነብዬ።
ከሄድኩማ ጥዬሁ
ስምሁን ወዲያ ብዬ፣
እኔው ነኝ የምከስር
እኔው ነኝ አንቱዬ።
አንቱማ ሙሉ ነሁ ማን መቶ ማን ቀርቶ፣
ካሚል መልከ ውቡ ከዩሱፉ ጎልቶ፣
ለእኔው እንጂ ክስረት ለራኩት ከሱና፣
አንቱማ አንቱ ነሁ መሙላትሁ የፀና።
ሶሉ አለ ነቢይ በእኒያ በተኳሉት፣
መኳለዎ ቀድሞ በውልደት ባማሩት፣
በወዳጅ ቤተሰብ በሙላው ጠቅላላ።
ይርከፍከፍ ሰለዋት በሊሳኑ ሁላ።
ተፃፈ-በፈትሁዲን ኡመር
1447ዐ.ሂ
.
.
.
#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
