🔷 መውሊድ ማክበር ኢስላም አያውቀውም
قال الحافظ ابن رجب :
" فكل من أحدث شيئا ونسبه إلى الدين ولم يكن له أصل من الدين يرجع إليه فهو ضلالة والدين بريء منه ، وسواء في ذلك مسائل الاعتقاد أو الأعمال أو الأقوال الظاهرة والباطنة "
جامع العلوم والحكم ( 2/128 )
🔹ኢብኑ ረጀብ አል ሐንበልይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –
" ማንኛውም ነገር ፈጥሮ ወደ ዲን ያስጠጋው በዲን ውስጥ የሚመለስበት መሰረት የሌለው ከሆነ እሱ ጥመት ነው ( የእስልምና) ዲን ከሱ የጠራ ነው ። ይህ ፈጠራ በዐቂዳም ይሁን, በአካል የሚሰራ ዒባዳም ይሁን , ግልፅም ንግግር ይሁን ድብቅ ንግግር እኩል ነው ።"
↪️ መውሊድ በቁርኣንም ይሁን በሐዲስ መረጃ የሌለው እንዲሁም የሶሐቦች ተግባርም ሆነ እስከ አራተኛው ክ/ዘመን የነበሩ የኢስላም ሊቃውንቶች ያልሰሩት ፈጠራ ነው ።
↪️ መውሊድን የጀመሩት የአላህና የነብዩ ጠላት የሆኑት ዑበይድይ ( ፋጢምይ) የሚባሉ ራፊዳዎች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች አመቱን ሙሉ የነሳራዎችንና የአይሁዶችን በአል የሚያከብሩ የነበሩ ነብዩን እንወዳለን በሚል የነብዩን ዲን ለማጥፋት የሚሰሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው ። በመሆኑም ኢስላም የመውሊድ በአልን አያውቀውም ። ሙስሊሞችም ከዚህ የጠሩ ናቸው ።
↪️ ነብዩን እወዳለሁ የሚል ከዚህ ተግባር ሊርቅ ይገባል ። ነብዩን በመውደድ ከሶሓቦች የሚበልጥ የለም ። በህይወታቸው ፣ በደማቸው ፣ በክብራቸው በገንዘባቸውም ጭምር ለውዴታቸው ዋጋ ከፍለዋል ። መውሊድ የነብዩን ውዴታ መግለጫ ቢሆን ኖሮ የሚቀድማቸው አይኖርም ነበር ። የወደዱትን እያመፁ ውዴታ የለም ። ነብዩን የሚወድ ሱናቸውን ይከተል ከቢዳዓ ይራቅ ። ካልሆ ራሱን እንጂ ማንንም አይጎዳም ።
http://t.me/bahruteka










