#የአራስነት_ድባቴ
#Share_it #Postparum_depression
ድባቴ በቀላሉ በምክር፣ በልዩ ልዩ _ አስደሳች ፕሮግራሞች ወይም በቀላል መድኃኒቶች የሚታከም ህመም ነው፡፡ ህክምናውን በቶሎ ካገኘሽ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጤናሽ ተመልሶ ደስተኛ እናት ትሆኛለሽ::
የአራስነት ድባቴ ህመም ከመቶ ሴቶች በአስሩ ላይ ይከሰታል፡፡ የአራስነት ድባቴ የሚከሰተው አንዲት አራስ ከተገላገለች ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡ ይህ ምልክትና ህመም የሚያጠቃው በአብዛኛው የመጀመሪያ ልጆቻቸውን የተገላገሉ እናቶችን ነው:: ከስነ-ልቦና ህመም ውስጥ አንዱ የሆነው የአራስነት ድባቴ ‹ማትርናለ ብሉ› ተያያዥነቱ ከሴትነትና ከአራስነት ጋር ብቻ ነው፡፡ መነሻውም ‹መልካም እናት ነኝ ወይስ ልሆን አልችልም በሚል የራስ ግጭት ነው፡፡ በአራስነት ድባቴ ተጠቅቻለሁ ብለሽ ካስብሽ ለብቻሽ አታብሰልስይው፡፡ ለቅርብሽ ሰው አውሪው ከባሰም ሐኪምና የስነ-ልቦና ሐኪም እንዲሁም የማህበረሰብ አማካሪ አነጋግሪ፡፡
የህመሞች ሁሉ የመጀመሪያ መፍትሄ በሽታውን በትክክል መለየትና እንደተጠቃሽ ማወቅ ስለሆነ፤ በአራስነት ድባቴ መጠቃት ወይም አለመጠቃትሽን በሚከተሉት ምልክቶች መረዳት ትችያለሽ፡፡
❖ ኃይለኛ ንዴትና ብስጩነት፣
❖ ከዚህ ቀደም ያስደስቱሽ በነበሩ ነገሮች ላይ ፍላጎት ማጣት ወይም መጥላት፣
❖ ተደጋጋሚ የሐዘን ስሜትና እምባ እምባ የሚልሽ ከሆነ፣
❖ ደክሞሽ እንኳን ለመተኛት መቸገር፣
❖ የተጋነነ የስሜት መለዋወጥ (በጣም ደስተኛ እና በጣም ሐዘንተኛ መሆን)፣
❖ ከአራስ ልጅሽ ጋር የመቆራኘት ስሜት ማጣት፣
❖ አብዝተሸ የምትጨነቂ ከሆነና የተጋነነ ስጋት ካደረብሽ፣
❖ ሐሳብሽን በአንድ ነገር ላይ ሰብስበሽ መስራት ከተቸገርሽ፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ምልክቶች ታይተውብኛል ብለሽ እራስሽን የአራስነት ድባቴ ተጠቂ አድርገሽ መውሰድ የለብሽም፡፡ ነገር ግን የድባቴ ምልክቶቹ፡-
1. ከሁለት ሳምንት በላይ ከቀጠሉ፣
2. እየባሱ ከመጡ፣
3. አራስ ልጅሽ ለመንከባከብ አዳጋች ካደረጉብሽ፣
4. የዕለት ተዕለት ተግባርሽ በአግባቡ ለማከናወን አቅም ካሳጡሽ እና
5. አእምሮሽ ልጅሽን ወይም እራስሽን ስለመጉዳት ማሰላሰል ከጀመረ ውለሽ ሳታድሪ ወደ ህክምና ተቋም ሔደሽ ባለሙያ ማማከር ይኖርብሻል፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት አንዱ ውስጥሽ ካለ ሐኪም ዘንድ መቅረብ ግዴታሽ ይሆናል፡፡
ስለ ህመሙ መደንገጥ አይጠበቅብሽም፡፡ ምክንያቱም ይህ ችግር በእርግዝና ምክንያት በሚመጣ የኬሚካል መዛባት የሚከሰት ነውና፡፡
ድባቴ በቀላሉ በምክር፣ በልዩ ልዩ _ አስደሳች ፕሮግራሞች ወይም በቀላል መድኃኒቶች የሚታከም ህመም ነው፡፡ ህክምናውን በቶሎ ካገኘሽ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጤናሽ ተመልሶ ደስተኛ እናት ትሆኛለሽ::
#Mental_Health #Awareness_Month
https://www.facebook.com/100002933256142/posts/7618202538287446/?mibextid=PYmHZq6NeoFKAokE
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
May 24, 2024 3K 1 10