የበረሃ እንባ 💔 [ የሊብያ በርሃ ] ​ክፍል 5 ​ፀሐፊ zoya~. የቀጠለ በአዲስ አበባ... ​የኦርሳም… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

የበረሃ እንባ 💔        [ የሊብያ በርሃ ]


​ክፍል 5

​ፀሐፊ zoya~.

የቀጠለ


በአዲስ አበባ...

​የኦርሳም ቤት በለቅሶ ታውኳል ጎረቤቶች ወይዘሮ ጀሚላን ለማረጋጋት ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም ሁለት ቀን ሙሉ እህል በአፋቸው አልቀመሱም ሀኪያ ራሷን ስታ ስለወደቀች በጎረቤት እርዳታ በአቅራቢያው ወዳለ ክሊኒክ ተወስዳለች እስካሁን ግን አልነቃችም ወይዘሮ ማሚቴ ደብዳቤውን ደረት ላይ አጣብቀው "ልጄ... አላህ ይዘንለት" ከማለት ውጪ ቃል አጥተዋል።
​በረሃው ግን ዝምተኛውንም ሆነ ጩኸታሙን እኩል የሚቀበል ጨካኝ መሆኑን ገና አላወቁም

​ደላሎቹ ሃያ ሶስቱን ወጣቶች ወደ ሌላ ትልቅና ክፍት መኪና ጫኗቸው አሁን የሚጠበቃቸው የሱዳን ሰፊውና አሸዋማው በረሃ ነው ፀሐይዋ ወደ መሬት ዝቅ ያለች ትመስላለች ውሃ ጥሙ ገና አሁን ጉሮሮውን መለብለብ ጀምሯል
​መኪናዋ አሸዋውን እየቀዘፈች ወደ መካከለኛው ሱዳን ስትገሰግስ ኦርሳም የኢዘዲንን ትከሻ ተደግፎ አይኑን ጨፈነ  በረሃው ገና 'ሀ' ብሎ ጀምሯል።

.....  ​መኪናዋ አሸዋውን እየቀዘፈች ወደ ፊት ትጋልባለች የሱዳን ንዳድ በመኪናዋ ብረት ላይ አልፎ ቆዳቸውን ይለበልበዋል ኦርሳም ጥሙ ጉሮሮው ላይ እንደ እሾህ እየወጋው ነው ምክንያቱም መንገድ ከጀመሩ ሁለት ሳምንት ሆኖዋቸዋል  የያዛትን ትንሽ ውሃ ለከፋ ቀን ብሎ ቆጥቧታል በአጠገቡ ያሉት ሶማሌዎችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በዝምታ ተውጠው  በሃሳብ ወደ ኋላ የቀሩ ቤተሰቦቻቸው ጋር ተጉዘዋል።

​ኢዘዲን የኦርሳምን ትከሻ ነካ አደረገውና በሹክሹክታ "ኦሪ... ይቺን ታይም ካለፍን በኋላ ሁሉም አሪፍ ሚሆን ይመስለኛል ግን ከዚህ በኃላ ካርቱም ነው መሰለኝ ምንሄደው " አለው።
​ኦርሳም የዛለ ድምፁን አውጥቶ "ኢዙ... ካርቱም ደርሰን ለቤተሰብ የምንደውልበት ቻንስ ይኖራል ይሁን ? እማ አሁን ምን ሆና ይሆን? ሀኪያ ስትነቃ የምታየው ወንድሟን ሳይሆን ያቺን የተረገመች ደብዳቤ ነው" አለ አይኖቹ በእንባ እያረሩ

​በአዲስ አበባ...

​ክሊኒኩ ውስጥ ያለው የኦክስጅን ማሽን ድምፅ ብቻ ይሰማል ሀኪያ አይኖቿን ቀስ ብላ ገለጠች በመጀመሪያ ያየችው ነጭ ጣሪያውን ነበር ቀስ እያለች ነገሮች ትዝ አሏት "ኦሪ!" ብላ ለመጮህ ሞከረች ግን ድምጿ አልወጣም እናቷ ወይዘሮ ጀሚላ አጠገቧ ተቀምጠው አይኖቻቸው በእንባ ደም መስለዋል ሁለት ሳምንት ሙሉ የልጃቸውን መጨረሻ ለማወቅ በጉጉት ሲጠብቁ ደክመዋል
​"ልጄ... ነቃሽልኝ?" አሉ ወይዘሮ ጀሚላ እጇን እየሳሙ

​ሀኪያ በምልክት "ወንድሜስ?" አለቻቸው  እናቷ መልስ አልነበራቸውም  ዝምታው ከጩኸት በላይ ሀኪያን አደቀቃት። ወንድሟ የእሷን ህይወት ለማዳን ሲል ራሱን ለሞት አሳልፎ እንደሰጠ ገባት። ክሊኒኩ ውስጥ ያለው አየር ለሀኪያ አልበቃም


​ፀሐይዋ እየጠለቀች ስትሄድ የበረሃው ቅዝቃዜ ደግሞ ሌላ መከራ ይዞ መጣ መኪናዋ ድንገት ፍሬን ይዛ ቆመች  ደላሎቹ በከፍተኛ ድምፅ እየጮሁ "ውረዱ!" አሏቸው።
​አንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ሰበሰቧቸው  ከፊት ለፊታቸው ትልቅ በርሜል ውሃ አለ  ሁሉም እንደ እብድ ወደ ውሃው ሲሮጡ ደላሎቹ በዱላ መምታት ጀመሩ።
​"بالترتيب! واحد واحد!"
"በተራ አንድ በአንድ! "እያለ ሱዳናዊው ደላላ ይጮኻል።
​ኦርሳም ተራው ደርሶ ውሃውን ሲቀምሰው ውሃ ሳይሆን ጨው ቀላጭ መሰለው "ኢዙ... ይሄ ውሃ ቴስቱ አይመችም" አለው ፊቱን አጨፍግጎ
​"ኦሪ... ይሄ ኖርማል ነው አሁን ኃይል እንዲኖረን ለ ነው የምንጠጣው። ጠጣው!" አለው ኢዘዲን ለራሱም እየቀፈፈው ።
​በመሃል ግን ከወጣቶቹ አንዱ በውሃው ጥም ብዛትና መንገድ ላይ  በወባ መያዙ መሬት ላይ እንዲዘረር አደረገ ። ደላሎቹ መጥተው በጫማቸው መቱት ግን ልጁ አልተንቀሳቀሰም ኦርሳም በድንጋጤ ወደ ልጁ ሊጠጋ ሲል ኢዘዲን ያዘው
​"አትሂድ ኦሪ  ሕጉ አይፈቀድም አይፈቅድም" አለው።
​ደላላው የልጁን ትንፋሽ አዳመጠና ለጓደኛው በንቀት
"خلاص، مات"
"በቃ ሞቷል" አለው።

ከዚያም እንደ አሮጌ እቃ ጎትተው ከሜዳው ወጣ አድርገው ጣሉት ኦርሳም የሰው ልጅ እንዲህ በቀላሉ ዋጋው ሲረክስ ሲያይ መላ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ
​"ዛሬ እሱን... ነገስ እኔን?" የሚል ጥያቄ በጭንቅላቱ ውስጥ እያስተጋባ ጉዟቸው በጨለማው ውስጥ ቀጠለ

መኪናዋ በበረሃው አሸዋ ላይ ስትጋልብ የሞተው ልጅ ምስል ከኦርሳም አይን አልጠፋም ነበር "ኢዙ... በቃ እንዲህ ነው የሰው ልጅ ዋጋው ከእንስሳም በታች የሚሆነው እዚህ በረሃ ላይ ነው?" አለው ድምፁ በመንቀጥቀጥ።

​ኢዘዲን ግን ራሱን ወደ ሰማይ ቀና አድርጎ "ኦሪ... አሁን ምንም ማድረግ አይቻልም  እኛ አላማችን ላይ ካልደረስን የዛ ልጅ እጣ ፈንታ ነው የሚጠብቀን ቆፍጠን በል" አለው። ምንም እንኳን ቃላቱ ጠንካራ ቢሆኑም የኢዘዲን አይኖች ግን ርህራሄና ፍርሃት ተቀላቅሎባቸዋል።

​በአዲስ አበባ...

​ክሊኒኩ ውስጥ ያሉት ወይዘሮ ማሚቴ ከሀኪያ አልጋ አጠገብ አንገታቸውን ደፍተው ተቀምጠዋል ሀኪያ አይኖቿን ወደ ጣሪያው ሰቅላ "እማ... ኦሪ ይርበው ይሆን ውሃስ አግኝቶ ይሆን?" ስትል ጠየቀች
​ወይዘሮ ማሚቴ የሀኪያን እጅ አጥብቀው ይዘው "አላህ ካለ ይደርሳል ልጄ ግን ይሄ በሽታሽ ነው እሱን ያስጨነቀው በዱአሽ አትርሽው" አሏት። በልባቸው ግን "ልጄን ማን ይረዳው ይሆን ?" የሚለው ጭንቀት እንደ እሳት ይበላቸዋል።


​ከቀናት አድካሚ ጉዞ በኋላ  በሩቅ የከተማ መብራቶች መታየት ጀመሩ ካርቱም የሱዳን መዲና ነገር ግን ይቺ ከተማ ለኦርሳም እና ለጓደኞቹ የእረፍት ቦታ ሳይሆን የባርነት ደጃፍ ነበረች
​መኪናዋ አንዲት ጠባብና አሮጌ መጋዘን ውስጥ ገባች አዲስ  የኢትዮጵያ ደላላ በሩን ከፍቶ ገባ ከዛ ደላሎቹን በአረብኝ ሞቅ ያለ ሰላምታ ካቀረበ በኃላ የሆነ ሰነድ ለአንዱ ደላላ አቀበለው ሰንዱን ካየው በኃላ የሱዳኑ ደላላ ወደ ወጣቶቹ ዞር ብሎ በአረብኛ ትእዛዝ አስተላለፈ

​"يا شباب، اسمعوا جيدا"
"ወጣቶች በደንብ ስሙ"

​ደላላው ተረጎመላቸው "አሁን ካርቱም ላይ ናችሁ ነገር ግን በነፃ የምታልፉ እንዳይመስላችሁ ለስድስት ወራት እዚህ ከተማ ውስጥ ለጉልበት ስራ ትሸጣላችሁ የምታገኙትን ገንዘብ ሁሉ ለደላሎቹ ታስረክባላችሁ ያ የሊቢያ መንገዳችሁ ክፍያ ይሆናል ማለት ነው።"

​ወጣቶቹ በድንጋጤ እርስ በእርስ ተያዩ "ስድስት ወር?" አለ ኦርሳም በሹክሹክታ "ኢዙ... ስድስት ወር ሙሉ ለነሱ ስንሰራ እማና ሀኪያ ምን ሊሆኑ ነው እኔ እኮ በወር ውስጥ እደርሳለሁ ብዬ ነው ደብዳቤ የፃፍኩት።"

​ኢዘዲን ራሱን ይዞ "ኦሪ... ይሄ ወጥመድ ነው። ግን አማራጭ የለንም። ከተቃወምን  እዚሁ ይገድሉናል። ቢያንስ ላይፋችንን ለማዳን መስራት አለብን " አለው።

​በማግስቱ ጠዋት ገና ፀሐይ ሳትወጣ ትላልቅ የጭነት መኪናዎች መጋዘኑ ደጃፍ ቆሙ የተለያዩ አሰሪዎች መጥተው ወጣቶቹን መምረጥ ጀመሩ ኦርሳም እና ኢዘዲን ተቃቅፈው እንዳይለያዩ ቢጠነቀቁም አንዱ የድንጋይ ከሰል አምራች ኦርሳምን ሲመርጠው ኢዘዲን ደግሞ ወደ አንዲት ትልቅ እርሻ ተመደበ
​"አይሆንም አብረን እንድንሆን ተነጋግረናል ፍቀዱልን " ኦርሳም በአረብኛ ባይሆንም በጩኸት ለመናቸው
​ነገር ግን ደላላው በዱላው ትከሻውን እየመታ አጣደፈው
"خلاص! اذهبوا!"
"በቃ ሂዱ " ብሎ በቁጣ አዘዘ።
🔥15❤10
September 3, 2026 1.7K 3