ክፍል 4
ፀሐፊ zoya~
..........መኪናዋ በድንገት ፍሬን ስትይዝ በመኪናው ወለል ላይ ተደራርበው የነበሩት ወጣቶች ትንፋሽ አብራ ቆመች የጎማው ፍጭት የቀሰቀሰው አቧራ በመስኮት በኩል ሰርጎ ገብቶ ሳላቸውን አውኮታል ፊት ለፊት ያለው ኬላ ላይ የቆሙት የታጠቁ ወታደሮች መኪናዋን በጥርጣሬ እየተመለከቱ ነው ኦርሳም በረጅሙ ተነፈሰ እናቱንና እህቱን ሳይሰናበት የወጣባት ያቺ ሌሊት የመጨረሻው ትዝታ ሆና ልትቀር እንደሆነ ሲያስብ ሽብር ወረረው ከፋው በውስጡ ዱአ ተያይዞታል
ሹፌሩ በሹክሹክታ "ማንም ቀና እንዳይል ድምፅ ያወጣ ሰው እዚሁ ይጣላል ሰምታችኅል " ሲል አስጠነቀቃቸው ሹፌሩ ከመኪና ወርዶ አንዱን ወታደር ትንሽ ካወራው በኋላ ሹፌሩ ጥቅል ብር አውጥቶ ለወታደሩ አቀበለው የሰው ልጅ ነፃነት በቆሸሸ የብር ኖቶች ተተመነ መኪናዋ ዳግም ሞተሯን አነሳሳች
በአዲስ አበባ...
......የጠዋቱ ፀሐይ በቆርቆሮው ቀዳዳ ሰርጋ ገብታ የሀኪያን ፊት ላይ አብለጨለጨች ሀኪያ በ
ሳል እየተናነቃት ተነሳችና "ኦሪ... " አለች በደከመ ድምፅ መልስ የሚሰጣት አልነበረም እናቷ ወይዘሮ ከውጪ እየገባች "ኦር ገና አልመጣም እንዴ ሥራ በዝቶበት ይሆናል በመጨረሻም ሥራው ከፈተለት ?" እያመሰገኑ አሮጌው ፍራሽ ላይ ተቀመጡ ግን ገና ጉዳቸውን አላወቁ
ሀኪያ መድሃኒት ልትወስድ ትራሷን ስታነሳ ያቺን የታጠፈች ወረቀት ወደቀች ግራ እየተጋባች ሳትከፍተው "እማ... ይሄ ምንድነው?" ብላ ለእናቷ ሰጠቻት እናቷም እየተቀበሏት "ምንድነው እስቲ አምጭው "ደብዳቤውን ከፈቱት አይናቸውን ወረቀቱ ጋር እያቀረቡ ማንበብ ጀመሩ ፊታቸው ቀስ በቀስ ተቀያየረ የቆሙበት መሬት የተሰነጠቀ መሰላቸው "ወይኔ ልጄ የት ሄድክብኝ ምነው ሁሉም በቀረብኝ ምን አደረኩ ?" እያሉ ጩሀታቸውን አቀለጡት የሀኪያ ራሷን መሳት ና የጎረቤት ድንጋጤ የቤቱን ፀጥታ አወከው
በመተማ በረሃ...
...... መኪናዋ መተማ ስትደርስ የታየው ግለትና አቧራ ለኦርሳም የጀሃነም ደጃፍ ይመስላል ሹፌሩ ማለትም አገናኙ ወጣቶቹን የሰው ሽታና የላብ ጠረን ወደሚገማ አንድ ጠባብ መጋዘን ውስጥ አስገባቸው ኢዘዲን ወደ ኦርሳም ጠጋ ብሎ "ኦሪ... ስሜቱ አይመችም ግን ፋራ እንዳትሆን ይቺ መከራ አልፋ ሸገር ስንመለስ ሲክስ ፔክ ሰርተን በዶላር ነው የምናብደው አለው ለማበረታታት እየሞከረ።
እስካሁን ዝምታን የመረጠው ኦርሳም ግን ራሱን እየነቀነቀ "አይ ኢዙ... ነገሩ ራሱ ፋራ አድርጎ እንዳይተወን ነው ምፈራው እዚህ ያለው ድባብ ላይፍ ሳይሆን ችግር እየሸተተኝ ነው" ብሎ መለሰለት
በወሬያቸው መሃል በድንገት በሩ በሃይል ተበረገደ ፊታቸው ላይ ጥልቅ ጠባሳ ያለባቸው ጥቁር ሀለታቸው የሚያስታውቅ ሱዳናውያን ደላሎች ገቡ ከደላሎቹ አንዱ ወደ ወጣቶቹ እየተጠጋ በሚያስፈራ ድምፅ ጮኸ
"يا الله! قوموا يا شباب"
"ተነሱ ወጣቶች "
ሹፌሩ ማለትም አገናኙ ወጣቶቹን እንዲነሱ አዘዛቸው
ደላሎቹ ልክ እንደ ከብት ገበያ እያንዳንዱን ወጣት በዓይናቸው እየመተሩ አለፉና ወደ አንድ ጥግ ከኢትዮጵያዊው ደላላ ጋር እያወሩ ሄዱና መደራደር ጀመሩ
"كم عددهم؟"
"ስንት ናቸው "
አገናኙም "خمسين"
ብሎ መለሰለት።
ሱዳናዊው ፊቱን አጨፍግጎ ወደ ወጣቶቹ እያመለከተ በድጋሚ ተናገረ
"معليش، العدد كبير. نقسمهم تلاتة وعشرين، تلاتة وعشري
ይቅርታ ቁጥሩ በዝቷል ሃያ ሶስት ሃያ ሶስት ከፋፍሏቸው
አገናኙ ወደ ወጣቶቹ ዞር ብሎ በደረቁ "ቁጥራችሁ ስለሚበዛ ለሁለት ትከፈላላችሁ የቀራችሁት ከሌላ ቡድን ጋር ትሄዳላችሁ እና ለአሁኑ ብር አያስፈልግም ወደፊት ግን መንገዳችሁ ላይ ያስፈልጋችኅል እና እየሰራችሁ መንገዱን ትገፋላችሁ " አላቸው።
ኢዘዲን የኦርሳምን እጅ አጥብቆ ያዘውና አየኸው ኦሪ ኩዊዝ ሊያደርጉን ነው። ችግር እንዳይመጣ ቆፍጠን ብለን በአንድ ጀማ መሆን አለብን ካልተለያየን እንወጣዋለን" አለው።
ኦርሳም "አዎ ልክ ነህ ብሮ መለያየት የለብንም አለው በስስት እያየው
ሱዳናዊው ደላላ ብር አውጥቶ እየቆጠረ
"كل واحد بكم؟"
"እያንዳንዱ ስንት ነው" ብሎ ሲጠይቅ የገንዘቡ መቆጠር የሰው ልጅ ዋጋ ተተምኖ እየተሸጠ መሆኑ ወጣቶቹ ግራ ቢገባቸውም አምነዋል ምክንያቱም ስኬታማ ለመሆን ብዙ መጓዝ አለባቸው
ደላላው ወደ ኦርሳም ጠጋ ብሎ አገጩን ይዞ ቀና አደረገው ዓይኖቹ ውስጥ ምንም ዓይነት ርህራሄ አይታይም። ለጓደኛው ዞሮ
"هذا سوف يكون قوي في الصحراء"
"ይሄኛው ጠንካራ ይመስላል " አለው።
ኦርሳም በመገፋት ወደ መኪናው ሲጫን ከኋላው የቀሩት ጓደኞቹ ኢዘድንን ጨምሮ አንድ ላይ እንዲደርሳቸው እየተመኙ ነበር ጉዞው አሁን በይፋ የሰው ንግድ ወደሆነበት የሱዳን በረሃ ተቀየረ
መኪናዋ ከፍ ባለ ድምፅ እየተንቀሳቀሰች መተማን ጥላ ወደ ሱዳን ድንበር ስትገባ የውስጧ ሙቀትና የታፈነው አየር መተንፈስ አቅቶታል ኦርሳም በመኪናው ብረት ላይ ተደግፎ የኢዘዲንን እጅ አጥብቆ ይዟል ያ የደላላው ቃል"ይሄኛው ጠንካራ ይመስላል"በጆሮው ላይ እንደ መርዶ ይደጋገምበታል ጠንካራ መሆን ያለበት ለራሱ ሳይሆን ለሚሸጡት ሰዎች ትርፍ እንዲያመጣ መሆኑን ሲያስብ ሰውነቱ ወረረው
"ኢዙ... ይሄ ነገር አልጣመኝም " አለ ኦርሳም ድምፁ እየተንቀጠቀጠ
ኢዘዲን ግን ፊቱ ላይ ያለውን ፍርሃት ደብቆ "አይዞህ ኦሪ መራራውን ጣፋጭ ነው ብሎ መቀበል ነው " አለው ነገር ግን የኢዘዲን እጆችም ይንቀጠቀጡ ነበር
ከሁለት ቀን ጉዞ በኋላ መኪናዋ ቆመች በረሃው ገና ሳይጀምር ንዳዱ ልብስ ይበሳል ደላሎቹ ወጣቶቹን ከእንቅልፍ እየቀሰቀሱ ከመኪናው ላይ እየገፈተሩ አወረዷቸው
"يا الله! بسرعة!"
" ያአላህ! ፍጥኑ"
የቡድን ክፍፍሉ ተጀመረ አገናኙ እንዳለው ሃያ ሶስት ሃያ ሶስት ሆነው እንዲቆሙ ተደረገ ከሌላ ቦታ የመጡ ሶማሌዎችም አሉ ኦርሳም እና ኢዘዲን ተቃቅፈው በአንድ ቡድን ውስጥ ለመሆን ቢሞክሩም ሱዳናዊው ደላላ ኦርሳምን በሃይል ጎትቶ ወደ ሌላኛው ቡድን ወረወረው
"አይሆንም እባክህ... አትለየን" ኢዘዲን ጮኸ
ኦርሳም የደላላውን እግር ስር ተደፍቶ በአማርኛ ይለምነው ጀመር "እባክህን... ወንድሜ ነው አትለየኝ የምትለኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብቻ አትለየን" ለመነው ደላላው አማርኛ ባይገባውም የኦርሳም አይኖቹ ውስጥ ያለው መማጸን ልቡን የነካው ይመስላል
ደላላው ለጥቂት ሰኮንዶች ትኩር ብሎ አየውና ወደ ሌላኛው ደላላ ዞሮ በአረብኛ እንዲህ አለ
"هذا سيكون معروفي الأخير ولطفي معكم"
"ይህ የመጨረሻው ውለታዬ እና ደግነቴ ይሁንላችሁ።"
ቀጥሎም አንዱን ረዳቱን ጠርቶ "አብረው ይሁኑ" በሚል ምልክት አዘዘው። ኢዘዲንና ኦርሳም ተመልሰው ተቃቀፉ
"ኢዙ... ተረፍን ብሮ! አብረን ነን" አለ ኦርሳም አይኑን እየጠረገ።
"አይዞህ ኦሪ... አንለያይም "አለው ኢዘዲን።
ክፍል 5 ከ 100👍 ľįķę ቡሃላ ይቀጥላል......


