ህዳሴ ሚዲያ ማዕከል Gidduugala Odeeffannoo Hiddaasee: post #1909 — TG.ME

እንኳን አደረሳችሁ!! ​ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ለት/ቤታችን መምህራን ፣ለተማሪዎቻችን፣ ለወላጆችና ለመላው የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ በሙሉ ​እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!! ​የጥምቀት በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት በዓል እንደመሆኑ መጠን ሁላችንም በደስታ ልናከብረው ይገባል። ሆኖም ግን፣ ውድ ተማሪዎቻችን በአሁኑ ወቅት በፈተና ዝግጅት ላይ እንደምትገኙ መዘንጋት የለባችሁም። በዓሉን ስታከብሩ የሚከተሉትን ነጥቦች በልዩ ትኩረት እንድትተገብሩ ትምህርት ቤታችን ያሳስባል፦ • ​ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፦ በዓሉን ስናከብር ለፈተና ዝግጅት የምንጠቀምበትን ውድ ጊዜ መሸርሸር የለብንም። በዓላዊ ስሜት ተገፋፍታችሁ ከጥናት ሰዓታችሁ እንዳትዘናጉ። • ​ከመጠን ያለፈ መዝናናትን ማስወገድ፦ መዝናናት ያለ ቢሆንም፣ ከፈተናው በኋላ ሰፊ የእረፍት ጊዜ ስላላችሁ አሁን ግን ቅድሚያ ለትምህርታችሁ እንድትሰጡ ይገባል። • ​ለወላጆች፦ ልጆቻችሁ በበዓሉ ሰበብ ከትምህርታቸው እንዳይዘናጉና በቂ የጥናት ጊዜ እንዲኖራቸው አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ​በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንልን እየተመኘን፣ ተማሪዎቻችን በፈተናችሁ ውጤታማ እንድትሆኑ ብርቱ ጥረት እንድታደርጉ በድጋሚ እናሳስባለን።           ​መልካም በዓል!! ​

January 19, 2026 4K 8