“ትምህርት በምንም ነገር አይደራደርም! የትምህርት ቤታችንን ጥራት በቀጣይነት ከማሻሻል ፈጽሞ ወደኋላ አንልም።
አሁንም ተጨማሪ ዘመናዊና ጥራት ያላቸው የትምህርት ቤት ፈርኒቸሮች ከቻይና ተጭነው ወደ ትምህርት ቤታችን በመምጣት ላይ ናቸው። ይህም ለተማሪዎቻችን የላቀ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር የምናደርገው ተጨማሪ ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው።
ነገር ግን የእኛ ራዕይ በህንፃና በፈርኒቸር ብቻ አይገደብም። መምህራኖቻችን፣ አመራራችን፣ የአሰራር ሥርዓታችን፣ ዲሲፕሊናችን፣ ቴክኖሎጂያችን፣ የማስተማር ጥራታችንና የተማሪዎቻችን ውጤት ሁሉ ከዚህ ኢንቨስትመንት ጋር በእኩል ደረጃ ማደግ አለባቸው።
መድረሻችን ግልጽ ነው — በዓለም ደረጃ የሚወዳደር ትምህርት ቤት!
ዓለም አቀፍ ደረጃ የሚለካው ባለን ህንፃና ፈርኒቸር ብቻ ሳይሆን፣ ተማሪዎቻችን ባላቸው ሥነ-ምግባር፣ ዕውቀት፣ ዲሲፕሊን፣ በራስ መተማመንና የላቀ የትምህርት ውጤት ነው።
በጥራት ላይ ድርድር የለም!
ቸልተኝነት የለም!
መቆም የለም!
በየቀኑ መሻሻል!
በሁሉም ነገር የላቀነት!”












