የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለወሰዳችሁ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ __ በነሀሴ 2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር የተሰጠውን… — HIVN Tech and Guidlines — TG.ME

የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለወሰዳችሁ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
__

በነሀሴ 2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር የተሰጠውን የጤና ሙያ የብቃት መዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከነሀሴ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባትና የብሄራዊ መለያ ቁጥር(FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 952 በስራ ሰዓት በመደወል ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በማሳወቅ ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፦    
1. በዚህ ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ ተመዛኞች በተናጠል የውጤት ትንተና (Domain analysis) ማየት የምትችሉ ሲሆን ይህም እራችሁን ለማሻሻል እና የበለጠ ለማብቃት እንደሚጠቅማችሁ መሆኑን እንገልፃለን።            
2. የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከሰኞ ዻጉሜ 2/2018 ዓ.ም ጀምሮ  ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል የሚላክ ስለሆነ የሙያ ፍቃዳችሁን 12ተኛ ክፍል በተማራችሁበት ክልል ማውጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
(ጤና ሚኒስቴር)

ለወቅታዊ ታማኝ የጤና መረጃዎች ⤵️
ቴሌግራም: https://t.me/addlist/IWOV6uABAi5lYTA0  ላይ ይከታተሉን::
ፌስቡክ: www.fb.com/tenachn
ዩትዩብ: youtube.com/@HIVN
ቲክቶክ: tiktok.com/@andu_tena
❤3
September 2, 2026 710 3