በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ "ህመማቸው እንደባሰባቸው" ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ለከፍተኛ ሕመም" መዳረጋቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ከጥቂት ቀናት በፊት ለሚዲያ አካላት አሳውቀዉ ነበር እስረኞቹ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ "የማያቋርጥ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው" ገልጸዋል። ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሁለቱ ግለሰቦቹ በሆስፒታል ይቆዩ ቢባልም "ያንን እምቢ ብለው በሰዓታት ልዩነት በማይመች መኪና ጭነው ወደ ማረሚያ ቤት መልሰዋቸዋል" ሲሉ የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ተናግረዋል። ግለሰቦቹ በ2015 ዓ.ም. ማብቂያ ላይ በአማራ ክልል ከተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ክስ ሳይመሠረትባቸው ለስድስት ወር ቆይተው ነበር። ከህግ ውጭ ለዚህን ያክል ጊዜ ተይዘው መቆየታቸው ራሱ አግባብ ባልሆነበት ለእንደዚህ አይነት አስከፊ ችግር እና እንግልት መሰጠቻው የገዢውን ፓርቲ ጭካኔ ይገልፅ ይሁን?? ©bbc @Goqaeth
December 24, 2024 1.3K 1