በአንደበት ቃሌ መሀል ዝም ያለ ጩኸት መልቶ፣
በእቅፌ እንባ ስፍር የሚናገር ቃል አውጥቶ፣
ከእቅፉ እንድገባ መሀል እጁን እንዳገኘው፣
ነፍሴን ከእጁ ስር ሰጥቶ መጣል ለተመኘው፣
አያይ ይሆን መጎስቆሌን ፣
አያይ ይሆን እንባ ቃሌን፣
በሕይወቴ እንዳነግሰው እንድሰጠው ሙሉ አካሌን፣
በፈለኩት በዳበሳ በወደኩኝ ከእግሩ ስር፣
ለእግሮቹ አፈር ትቢያ መዳበሻ በሆነልኝ የኔ ጸጉር፣
በደረስኩኝ ቀራንዮ፣
ፍቅሩ ገብቶኝ ባልኩኝ ወዮ፣
በተገኘው ካረፈበት፣
ሽቱ ይዤ ላፈስበት፣
ከዚህ ሁሉ ልቡና ጋር ወደቤቱ ብገሰግስ ፣
እላለሁኝ ስለሐጢአቴ ተንበርክኬ አንዴ ባለቅስ፣
ሙቅ እቅፉን በቀመስኩት፣
ችንካሮቹን ግርፋቱን ከዮሐንስ ጋር ባየሁት፣
በተጠጋሁ ከደረቱ፣
በዝሙቴ ብሰለጥን ባደረገኝ ጎበዝ ብርቱ፣
አያይ ይሆን መጨነቄን፣
ስለ ሀጢያት ስጥል ጨርቄን፣
አያይ ይሆን ዘበት ህልሜን፣
በመቅደሱ የፈለኩት ያን መቆሜን፣
አይሰማ ይሆን ዝም ብዬ ሳነባበት፣
አይሰጠኝም ያን ምኞቴን የኔን መሻት፣
ሊቀ ካህን የታመነው የኛ አባት፣
አስወጥቶ አይሰዳቸው ከልባቸው ለፈለጉት።
ቀን 8/9/2018
በ ኃይለ ሚካኤል
አቤል


