በዚህ ረገድ ሰዎች የፖለቲካ አቋማቸውን ለመቀየር የተራዘመና በጣም አስቸጋሪ የሆነ የእስር ዓመታት ማሳለፍ የሚጠበቅባቸው ለምንድነው? የሚለውን የmorality ጥያቄ ግን ላንባቢያን መተው የሚገባ ነው። የሆነው ሆኖ፣ እዚ ላይ አንድ ትዝብት አንስተን እንለፍ፥ ጸሃፊው ቀድሞ ይደግፈው የነበረውን የኦሮምያ መገንጠል ሃሳቡን የተወው፣ “ኦሮምያ ከኢትዮጵያ ቢገነጠል ሰላም አያገኝም” ከሚለው የቆየ መከሪያከሪያ ነጥብ ተነስቶ ነው። በኔ እይታ ይሄ ምክንያት ከኦሮምያ ነጻነት ተቃዋሚች (ለምሳሌ የታወቁቱ ጸረ ኦሮምያ አቋም የሚያራምዱ የፖለቲካ ቡድኖች) ሲመጣ የሚጠበቀው የተቃራኒ ወገን negativist tactic ይሆናል። ልክ ልጆችን ለማስፈራራት “ይሄን ካደረክ ጆሮ ቆራጩ ይመጣብሃል” እንደሚባለው ዓይነት መሆኑ ነው። ይሄው ምክንያት ከነ ኦቦ ጋዲስ ዓይነት ካሉት የቀድሞ የኦነግ ታጋዮች ዘንድ ሲመጣ ደግሞ defeatist argument ይሆናል። ይልቅ ኦሮምያ የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ውስጥ ቢቆይ፣ እንዴት ሁለንተናዊ ጥቅሞቹ በላቀ ደረጀ ሊከበሩ እንደሚችሉ ተንትኖ በማሳየት መገንጠል ብዙ ፋይዳ ያለው ነገር አለመሆኑን በመቂ መንገድ ማሳየት አይቻልም ወይ?
ፋ) ጸሃፊው ኦቦ ጋዲሳ፣ እስከ አስረኛው ምራፍ የኦሮሞ ብሄተኝነት ቆቡን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ያወልቅና በቀጣዮቹ ምራፎች በሌላ መልኩ ይከሰታል። በታሪክ ውስጥ በነበረ ቤተሰባዊ መስዋዕትነት ላይ ጭምር የቆመ የድሮ Ethiopian Nationalist፣ የግብጽን ታሪካዊ ጸረ—ኢትዮጵያ ተንኮሎች የሚያጋልጥ geopolitical analyst፣ የመጪው ዓለም የስነህዝብ እድገትና የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብት መመናመን ላይ science alarmist ብሎም የጠቅላይ ምንስትር አብይ አህመድ ደጋፊ optimist (not to say propagandist) ወዘተ ሆኖ ይታያል። ይመቸው። እውነት ለመናገር በተለይም የኋላኛው ነጥብ ግን ትኩረቴን ሳይስበው አልቀረም። ያው “ብልጽጌ ብልጽጌ እየተጫወተ ስለሆነ በደንብ እርገጠው” የምትል ማሳሰቢያ ደርሶኝም የለ? ጸሃፊው በተለይም በአስራ ዘጠነኛውና በሃያኛው ምራፎች ለጠቅላይ ምንስትሩ ያለውን ትልቅ ድጋፍ በግልጽ ያሳያል። በውነቱ ያወድሳል ወይም ያሸበሽባል ሊባልም ይችላል።
ይህ በንዲህ እንዳለ፣ ሃያ አንደኛው ምራፍ ውስጥ “የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተኑ” ያላቸውንና ጠቅላይ ምንስትሩ ላይ የሚስተዋሉ “አስደንጋጭ ውስንነቶች” በሚል የቀረቡት ትንተናዎች ግን ጸሃፊው some sense of balanced view ያለው ስለመሆኑም የሚያሳዩ ናቸው ብዬ ገምታለው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ የከፋ ድህነት አሁን ያለው መንግስት ሲመጣ ከነበረበት 25 በመቶ አካባቢ ዛሬ ላይ ወደ 43 በመቶ ከፍ እንዲል ያደረገውን የአይኤምኤፍ ፖሊሲ ፕሪስክሪፕሽን ተቀብሎ ስራ ላይ ማዋል፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁናቴ እጅግ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለውን የሙስና ችግር ባሳማኝ ትንተናዎች አስደግፎ ያቀረበበት ሂደት ይሄንኑ ነጥቤን የሚያጠናክር ነው። እነዚህን ጨምሮ ሌሎች እጅግ አስከፊ ችግሮች እጫንቃው ላይ ስለተጫነበት ህዝቡ መኖር አቅቶታል፤ አስቸኳይ መፍትሄ ይሻል ባይ ነው ደራሲው።
ጋ) ከላይ በተጠቀሰው የመጽሃፉ ሃያ አንደኛው ምራፍ ውስጥ አንድ ወሳኝና እንደ አንባቢ ትኩረቴን የሳበ ጥያቄ ያነሳል ደራሲው። “እነዚህ አስደንጋጭ ችግሮች እያሉ፣ ህዝቡ ለምን ከሁከት ተቆጥቦ ሸክሙን በትዕግስት ይሸከማል?” …. ጸሃፊው ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ ምላሽ ይሆናሉ ያላቸውን አምስት ምክንያቶች አስቀምጧል። ትኩረቴን የሳበው ግን ሁለተኛው ሲሆን፣ ይኻውም “ከተቋሟዊ አፈጻጻም ይልቅ ህዝቡ በመሪው ላይ ያለው እምነት” የሚለው ነው። እዚ ላይ ህዝቡ ምንም’ንኳ እጅግ አስከፊ ሁናቴ ውስጥ ያለ ቢሆንም ቅሉ፣ ስርዓቱ ላይ እስካሁን ያላመጸው “በመሪው ዓላማና በተቋሟዊ ብልሽት መካከል ያለውን ልዩነት ስለሚገነዘብ ነው” ባይ ነው ኦቦ ጋዲሳ። ይሄ ነጥብ “እኔ የምደግፈው ጠቅላይ ምንስትር አብይን እንጂ የብልጽግና ፓርቲ መንግስትን አይደለም” ያለንችንን አንዲት ወዳጃችንን የሚያስታውሰኝ ነው። እዚህ ላይ አንድ የመጽሁፉ አንባቢ ሊያነሳ የሚችለውን የpolitical morality ጥያቄ አንስተን እንለፍ፥ አንድ ለፖለቲካ አቅመ አዳም የደረሰ ሰው (ህዝብ ላለማለት) በህግ ተቋቁመው በህግ ከሚሰሩ ሃገራዊ ተቋማት ይልቅ ባንድ ግለሰብ መሪ ላይ እምነት የሚያሳድር ከሆነ፣ ያ ሃገር በርግጥም ሃገር ሊባል ይችላል ወይ? ወይም እንደሃገር ሊቀጥል ይችላል ወይ?
በነገራችን ላይ ይሄን ኢትዮጵያ እንደሃገር የገባችበትን አደገኛ ቅርቃር ጠቅላይ ሚንስትሩም በደንብ የተረዳው ይመስላል። ለዚህ ማሳያ የሚሆን አንድ ምሳሌ እናንሳ። ስድስተኛው ምርጫ ተደርጎ፣ ብልጽግና ፓርቲ ሙሉ በሙሉ አሸነፍኩ አለ። ኋላ ጠቅላይ ምንስትሩ ፓርላማ ላይ ካቢኔውን ሲያቋቁም፣ ምርጫ ተወዳድሮ የወደቀው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ምንስትር ሆኖ መሾሙን አንዲት የፓርላማ አባል በግልጽ ወጥታ ተቃወመች። “ህዝብ መርጦኝ ነው እዚ ያለውት” የሚል ነጥብ አስገብታ ነበር በንግግሯ።
የፓርላማ አባሏ የፕሮፌሰሩን ሹመት የተቃወመችበት ምክንያት አሳማኝ ሊባል የሚችል ነበር። የፓርላማ አባሏ ራሷ በትምህርት አስተዳደር መስክ PhD ያላት ነበረች። ብርሃኑ ነጋ ግን በትምህርት አስተዳደር ምንም ዓይነት መደበኛ ስልጠና የሌለው ብቻም ሳይሆን፣ የኮሌጅ ዲን ሆኖ ስለመስራቱ እንኳ ምንም ማስረጃ የለም። እንዲያውም አሜሪካ ኢኮኖሚክስ ኮርሶችን ከሚያስተምርበት ኮሌጅ ለቆ ኤርትራ በርሃ በመውረድ የታጠቀ አማጺ ቡድን መሪ ሆኖ የነበረ ስለሆነ፣ ሹመቱ ልክ አይደለም የሚል ነበር የፓርላማ አባሏ ነጥብ። ከተቋማዊ የሙያ አሰራርና እሳቤ አንጻር ሲታይ የፓርላማ አባሏ ትክክል ነበረች። ጠቅላይ ምንስትሩ በዛ የፓርላማ ስብሰባ ላይ የሰጣት መልስ ግን በዚህ ረገድ revealing ሊባል የሚችል ነበር። “ህዝብ አንቺን የት አውቆ ይመርጥሻል? እኛን አይቶ እንጂ” ነበር ያላት ጠሚው። በዚ ምላሽ የፓርላማ አባሏ ደንግጣ አማተበች። ያቺ የፓርላማ አባል አሁን ያለችው የት ይሆን? ባለችበት ሰላሟ ይብዛ!
ሃ) በመጨረሻም፣ መጽሃፉ ምንም’ንኳ አንባቢዎች ሊማሩባቸው የሚችሏቸውን በርካታ ጠቃሚ ጭብጦች (substantive points) አጭቆ ያቀረበልን ቢሆንም ቅሉ፣ የአርታዊ (editor) ዓይን ያላየው መሆኑ ግን በግልጽ የሚታይ ነው። መጽሃፉ እንደመጽሃፍ ሳይሆን ዝም ብሎ እንደ ተራ ጥራዝ ነገር ስለታተመ፣ የመጽሃፉ አዲስ ምዕራፍ ባሮጌው ምዕራፍ የመጨረሻ ገጽ አጋማሹ ላይ ታትሞ ልታገኙት ትችላላቹ። ብዙ ጊዜ የፖለቲካ ሰዎች መጽሃፍ ሲያሳትሙ፣ ለይዘቱ የሚጨነቁትን ያህል መጽሃፉ ስታንዳርድ ፎርማት ይዞ እንዲታተም በማድረግ ረገድ የሚያሳዩት ስንፍና ሁሌም የሚገርመኝ ነገር ነው በውነቱ። ደራሲው ኦቦ ጋዲሳ በመጽሃፉ ቀጣይ ህትመት ይሄን ነገር ያስብበታል በሚል ተስፋ አስተያየቴን በዚሁ እቋጫለው።
ኢ) መጽሃፉን እንድታነቡት እጋብዛለው። አመሰግናለው።
~ ተጻፈ በ ግርማ ጉተማ 👀🙏✌️!
ይሄን መጸሐፍ በ "PDF" በዚህ የቴሌግራም ቻናላችን ላይ በቅርብ ቀን ....!!📖📚🤘
እስከዛ ድረስ ቻናሉን "JOIN" እያደረጋችሁ ጠብቁን!!👌
.
.
.
📌 t.me/Fastsinfo99
🌴 🌴 🌴
Telegram
𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
✅|| 𝐘𝐀𝐀𝐃𝐀 ykn komii yoo qabaattan nuuf barreessaa.
✅|| ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካለዎት ይፃፉልን
✅|| write to us if you have any comments or complaints.
👀 @Fastmereja_Bot 👀

2September 7, 2026 421 1