እኔ ጀዋር ላይ ያቀረብኳቸው ክሶች አራት ነበሩ :-
1ኛ. የታጣቂ ሃይሎችን ትብብር ተቃውመሃል የሚል ነው። እሱ ግን "አልተቃወምኩም ÷አልደገፍኩም" ብሎ ነበር። አንተ ጋር መጥቶ ግን 99.9% ሲቃወም ነበር።
2ኛ. የመሪ እንጂ የመንግስት ለውጥ እንዲመጣ አትፈልግም ብዬዋለሁ። እሱንም መጥቶ በይፋ አረጋገጠ። እንኳንስ መንግስት እንዲወርድ ÷ እንዲዳከም አይፈልግም። የኦህዴድ ብልጽግና ወደ ድርድር እንዲመጣ አልያም መፈንቅለ-መንግስት እንዲካሄድ የሚፈልገው።
3ኛ. በተቋም (institution) አታምንም ነው ያልኩት። መጥቶ "እኔ .. እኔ" እያለ ሲያወራ የነበረው። አሁን ላይ ጀዋር ከማንም ጋር እየሰራ አይደለም። ያቺ ምኞቱ እንድትሳካና እድሉን ለመሞከር ብቻውን እየተንቀሳቀሰ ነው።
4ኛ. ሌላው ነገር ጀዋር የኢትዮጵያ ሕዝብ የህልውና ችግር የለበትም ብሎ ያምናል። ታጣቂዎቹ የህልውና ችግር እንዳለባቸው አያምንም። ይሄን አሳንሶ "የሰላም ጥያቄና የኢኮኖሚ መበላለጥ" አድርጎ ያስቀምጠዋል። አሁን ላይ የህልውና ጥያቄ አለበት ብሎ የሚያምነው "የኦህዴድ ብልጽግናን" ነው። የህልውና ችግር አለበት አናፍርሰው ÷ ካፈርስነው እንጎዳለን እያለ ነው። ጀዋር already ያቀረብኳቸውን ክሶች መልስ ሰጥቷል። አረጋግጦልኛል።
🗣️ልደቱ አያሌው🤘

September 7, 2026 333