#እየተነጋገርን ነው ግን ኦባሳንጆ ገለልተኛ ናቸው አናምንም" .. ብሏል ህወሓት ... ርግጥ ነው ኦባሳንጆ አርጅተዋል። በቢያፍራ የዘር ማጥ ፋት ወንጀልም ይከሰሳሉ። እርጅና አለ። አዲስአበባ ላይ የተሰጣቸው የተንጣለለ ቪላ ቤት በጥቅም ሊደለሉ እንደሚችሉ ሊያስጠረጥርም ይችላል።
የአለም ሀያላን ሀገራት ኦባሳንጆን እንደ አደራዳሪ የመረጡበት ምክንያት የፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ ሚና ስላላቸው ይህንን እንዲያስቀጥሉ ታስቦ ነው። የኬኒያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በአሁኑ ድርድር ትልቅ ሚና እንዲኖራቸው የሀያላን ሀገራት ፍላጎት በመኖሩ የገለልተኛ አደራዳሪ ጉዳይ የሚፈታበት እድል ሰፊ ነው።
የሆነው ሆኖ ... ህወሓት ለሰላም ድርድር ፍላጎት እንዳለው ፣ በኦባሳንጆ የተጀመረ ንግግር መኖሩን አምኖ መግለጫ ማውጣቱ የሚበረታታ ነው 🙏 *^%
.
.
.
3September 6, 2026 352 1