በነገራችን ላይ በፕሪሚየር ሊጉ ለአመታት ሲተገበር የቆየው የPSR መመሪያ እንደቀረ ታውቃላችሁ?
ፕሪሚየር ሊጉ የክለቦቹን ፋይናንስ በደንብ ለመቆጣጠር እንዲችል ለአመታት ሲተገብር የቆየውን PSR ትቶ አዲስ Squad Cost Ratio እና SSR የተባሉ መመሪያዎችን ከዚህ የውድድር ዘመን ጀምሮ ይተገብራል።
- PSR ምን ነበር?
PSR በሊጉ የሚወዳደሩ ክለቦች በሶስት አመት ውስጥ ከ105 ሚሊየን ፓውንድ በላይ እንዳይከስሩ የሚገድብ ህግ ነበር።በPSR የክለቡ ሁሉም አይነት ፋይናንስ ስሌት ውስጥ የሚገባ ነበር።
- በPSR የተተኩት Squad Cost Ratio(SCR) እና Sustainability and Systematic Resilience ምንድን ናቸው?
SCR ክለቡ ከሚያገኘው ከእግር ኳስ ጉዳዮች ጋር ከተያያዘው ገቢ ውስጥ 85% ያህሉን ለSquad ወጪ እንዲያወጣ ይፈቅዳል። ክለቦች በአንዳንድ ጉዳዮች እስከ 115% እንዲያወጡ ቢፈቀድላቸውም ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
በምሳሌ ስንመለከት አንድ የሆነ ክለብ በዚህ አመት ከእግር ኳስ ጋር በተያያዘ ያገኘው ገቢ 100 ሚሊየን ፓውንድ ቢሆን ለተጫዋቾች ደመወዝ፣ ለአሰልጣኞች ክፍያ እና ለሌሎች ከስኳዱ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ማውጣት የሚችለው 85 ሚሊየኑን ብቻ ነው።
SSR ደግሞ ክለቦች በየወሩ ቢያንስ 12.5 ሚሊየን ፓውንድ ካሽ እንዲይዙ የሚያስገድድ ሲሆን እዳቸውም ካላቸው ንብረት አንፃር ከ90% እንዳያልፍ ይከለክላል።
በዚህ የውድድር መስኮት ክለቦች ስንትም ቢያወጡ እንደበፊቱ በPSR የትርፍና ኪሳራ የማይዳኙ ሲሆን ክለቦች አሁን ላይ የሚጠነቀቁት ስለ እግር ኳሳዊ ገቢያቸውና ለስኳዳቸው ስለሚከፍሉት የገንዘብ መጠን ነው።
ህጉን የጣሰ ክለብ እንደ PSR 3 አመት መጠበቅ ሳያስፈልግ በአመቱ መጨረሻ ቅጣትም ለመቅጣት ያስችላል።
SHARE | @FN_SPORTS

9
5September 2, 2026 2.7K 1