FN SPORTS በኢትዮጵያ™: post #190896 — TG.ME

አርሰናል ከ አስቶን ቪላ?

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት የመዝጊያ ጨዋታ አስቶን ቪላ ከ አርሰናል የሚያገናኘው ጨዋታ ዛሬ ከምሽቱ 4:00 ይደረጋል።

ሁለቱ ክለቦች በባለፉት 5 የእርስበርስ ግንኙነታቸው ተመጣጣኝ ውጤት ያላቸው ሲሆን እያንዳንዳቸው 2 ጊዜ ሲያሸንፉ በቀሪው 1 ጨዋታ ነጥብ ተጋርተዋል።

ከሻምፒዮኖቹ በኩል የቡድኑ የኃላ ምሶሶዎቹ ዊሊያም ሳሊባ እና ጁሪየን ቲምበር በጨዋታው እንደማይሳተፉ ተነግሯል።

ጨዋታውን የ40 አመቱ አውስትራሊያዊው ዳኛ ጃረድ ጊሌት የሚመራው ሲሆን ዳኛው አርሰናልን በመራባቸው 10 ጨዋታዎች መድፈኖቹ 7 ጊዜ ድል ማድረግ ችለዋል።

ሁለቱም ክለቦች በሁሉም ውድድር በታሪክ 207 ጊዜ እርስበርስ የተገናኙ ሲሆን አርሰናል 89 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ወስዷል።

ከለንደን በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ርቃ በምትገኘው የበርኒግሀም ከተማ ቪላ ፓርክ 208ኛውን የአስቶንቪላ እና የአርሰናል ግንኙነት ማን ያሸንፋል? ግምታችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡ! 👇

SHARE |  @FN_SPORTS
❤8🔥6
August 31, 2026 1.2K 1