ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አመራርና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ
**
ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰንዳፋ
ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች የሙያ ክህሎትና የማስፈጸም አቅምን ለማሳደግ ያለመ ሥልጠና በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተሰጠ። በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው እና የዩኒቨርሲቲው የወንጀል መከላከልና ሕዝብ ደህንነት ኮሌጅ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ከበደ ደበሌ ተገኝተው፣ የመዲናዋን የትራንስፖርት ዘርፍ ለማዘመንና የትራፊክ ደህንነትን ለማረጋገጥ የአመራሩና ባለሙያው ብቃት ማደግ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ የሁለቱ ተቋማት አጋርነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
20September 1, 2026 1.7K









