በግንባታ ብረት ላይ የሚፃፈው B500DWR ምን ማለት እንደሆነ ያውቃሉ? ​በግንባታ ቦታ ላይ የምንጠቀማቸው… — Ethiopian Construction Vacancy & Tender — TG.ME

👉 በግንባታ ብረት ላይ የሚፃፈው B500DWR ምን ማለት እንደሆነ ያውቃሉ?

​በግንባታ ቦታ ላይ የምንጠቀማቸው የሪባር (Rebar) ብረቶች ላይ የተፃፉት ፊደላትና ቁጥሮች የብረቱን ጥንካሬ፣ የመታጠፍ አቅም እና የምህንድስና ስታንዳርድ ይነግሩናል።

🌟​የ B500DWR ትርጉም በዝርዝር፦

​- B (Reinforcing Steel): ለኮንክሪት ማጠናከሪያነት የሚያገለግል የስትራክቸር ብረት መሆኑን ያሳያል።

​- 500 (Yield Strength): የብረቱ የመሸከም አቅም ወይም Yield Strength 500 MPa መሆኑን ይገልፃል።

​- D (Ductility Class D): ከፍተኛ የመታጠፍና የመለጠጥ አቅም (High Ductility) ያለው መሆኑን ያሳያል። በተለይም የመሬት መንቀጥቀጥን (Seismic Load) ለመቋቋም ለሚሰሩ ህንፃዎች ተመራጭ ነው።

​- W (Weldable): ብረቱ በቀላሉ የሚበየድ (Weld የሚደረግ) እና በብየዳ ወቅት ጥንካሬውን የማይጣጣ መሆኑን ያመለክታል።

​- R (Ribbed Bar): ከኮንክሪት ጋር በጥሩ ሁኔታ እንዲጣበቅ (Bonding) ተደርጎ በካራ የተሰራ (Deformed Bar) መሆኑን ያሳያል።

​በእናንተ ሳይት ላይ አብዛኛውን ጊዜ የትኛውን የብረት ግሬድ (Grade) ታወጣላችሁ?


@etconp
❤7🥰4👏1
September 2, 2026 1.9K 12