28ኛ ቀን
ይህ ለምን ሆነ?🤔 አይባልም። እንዴት ይሆናልም አንልም። እግዚአብሔር ሥራው ግሩም ነው፥ ከአሳባችን በላይ ነው። ሁሉን ስለሚችለው አምላካችን ክብር ይሁን። ለእኛ ለሰው ልጆች ሰላም። 18/12/2018 ዓ.ም የዕለቱ መልእክት እነሆ፦
🙏❤🙏ጥሶ መውጣት ይሆናል!!🙏❤🙏
በመውለጃዋም ጊዜ እነሆ መንታ ልጆች በሆድዋ ነበሩ። ስትወልድም አንዱ እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም ቀይ ፈትል ወስዳ በእጁ አሰረች፦ ይህ መጀመሪያ ይወጣል አለች። እንዲህም ሆነ፤ እጁን በመለሰ ጊዜ እነሆ ወንድሙ ወጣ፤ እርስዋም፦ ለምን ጥስህ ወጣህ? አለች፤ ስሙንም ፋሬስ ብላ ጠራችው። ከእርሱም በኋላ ቀይ ፈትል በእጁ ያለበት ወንድሙ ወጣ፤ ስሙም ዛራ ተባለ። ዘፍ 38:27-30
🤲 እግዚአብሔር እንደ ቃሉና እንደ ፈቃዱ ከቀደሙት ያስቀድማችሁ።
🤔 ቃል እያላችሁ የቀደመውን፣ በር የዘጋባችሁን በችሎታው ገለል አድርጎ ያስቀድማችሁ።
👉 ይህ ዓመት ሳያልቅ ሰዎች እንዴት? ለምን? በምን መንገድ? የሚሉትን መቅድም ያድርግላችሁ።
🧎♂️መልካም ፆምና ጸሎት 🤲🤲🤲
👨👩👧 ሁላችሁንም ❤ው❤ድ❤ድ❤
🙌 ተባረኩ🙌🙌🙌
August 24, 2026 112 1