የደብረ ታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችን ያቀፈ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡ #EIPC ነሃሴ 21 .2018 ዓ.ም ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዘርፉ ባሳየው ከፍተኛ የስራ አፈፃፀምና መነቃቃትን ጨምሮ አጠቃላይ በኮሌጁ ባስመዘገባቸው ተጨባጭ ውጤቶች ጋር ተያይዞ በርካታ ኮሌጆች ተቋማችንን መዳረሻቸው እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን በዚህም የደብረ ታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች ጭምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ተገኝተው የስራ ልምድ ልውውጥ ማካሄድ ችለዋል:: ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ጨምሮ ጠቅላላ የተቋም አፈፃፀም በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኮሌጁ ዲንኖች እና EASE ፕሮጀክት አስተባባሪ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል:: ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው ገለፃና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻነት በነበረው ማጠቃለያ ውይይትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው በሚገኘው ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ ያሳየው የላቀ አፈፃፀም በሌሎች አቻ ኮሌጆችም ጭምር ሞዴል ተደርጎ እንዲታይ ያስቻለው መሆኑንም ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን ማድረግ ችለዋል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa): post #6066 — TG.ME
August 27, 2026 516 1









