Ethiopian Coffee and Tea Authority: post #7374 — TG.ME

የ 2018 የቡና አጠቃላይ ሁኔታ
ብዙ መዋዠቅ፣ ማገገም እና ትራንስፎርሜሽን የተስተዋለበት ዓመት
 
2018 ዓ.ም ለዓለም አቀፍ የቡናው ኢንዱስትሪ ወሳኝ አመት ሆኖ እየተገባደደ ይገኛል፡፡ አዲሱ የምርት ዘመን እንደመጀመሩ እስቲ 2018 ዓ.ም  ምንን አስመልክቶን እንዳለፈና ይህ ለቀጣይ ምንን እንደሚያመላክት  እንመልከት፡-
 
ዓለማቀፍ የአቅርቦት ሁኔታ፡-
USDA በመባል የሚታወቀው የአሜሪካ የልማት ድርጅት መረጃ እንደተነበየው 189.7 ሚሊዮን 60 ኪ.ግ ኬሻ ቡና በ2018/19 ለዓለም ገበያ ይቀርባል፤ ከዚህም 105.9 ሚሊዮን አረቢካ፣ 83.8 ሚሊዮን ሮብስታ ይሆናል፡፡ ከቡና ተጠቃሚዎች አንጻር ዓለማቀፍ የቡና ፍጆታ 179.7 ሚሊዮን ኬሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
ዋነኛ አምራች አገራት፡-
ብራዚል፡- 71.9 ሚሊዮን ኬሻ ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የአየር ንብረት ሁኔታ ችግር እንዳለ ሆኖ ይህ ምርት ሪከርድ የሰበረ ምርት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ቬትናም፡- 32.5 ሚሊዮን ኬሻ፡፡ ከዚህ መካከል 31.4 ሊዮን ሮብስታ ቡና ይሆናል፡፡ የቬትናም የምትልከው ቡና እየጨመረ የመጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ኮሎምቢያ፡- 13.4 ሚሊዮን ኬሻ ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ቢሆንም ቡዌናቬንቱራ የተባለ አካባቢዋ የነሐሴ ወር የመሬት መንቀጥቀጥ መንገዶቿና ሎጂስቲኮቿ ላይ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ (ይህም የማምረትና የምርት ማጓጓዟ ላይ እክል ይፈጥራል ተብሎ ይሰጋል፡፡)
ኢትዮጵያ፡- 12.1 ሚሊዮን ኬሻ ቡና ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በውጭ ምንዛሪ ረገድ ደግሞ 3 ቢሊዮን ዶላር ታስገኛለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (እንደሀገራችን እቅድ ደግሞ 4 ቢሊዮን ዶላር ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡)
ኡጋንዳ፡- 7.2 ሚሊዮን ኬሻ፡፡ አገሪቱ በ2030 ዓ.ም 20 ሚሊዮን ኬሻ ቡና ለማምረት አልማለች፡፡
ኢንዶኔዢያ፡- ከመጠን በላይ በዘነበው ዝናብ ምክንያት የዚህች ሀገር የቡና ምርት ወደ 11.4 ሚሊዮን ኬሻ ዝቅ ይላል ተብሎ ተገምቷል፡፡
 ሕንድ፡- የአየር ንብረት ጫና እያለባት 6.1 ሚሊዮን ኬሻ ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሆኖም ቀጣይነት ያለው የሕንድ ቡና ፍላጎት እየተስተዋለ የመጣ ጉዳይ ነው፡፡
ሁንዱራንስ፡- ከ6 ሚሊዮን ኬሻ የተሻገረ ቡና ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፔሩ፡- የዝናብና የቡና በሽታ ችግሮች ተጋርጠውባት 4.8 ሚሊዮን ኬሻ ታመርታለች ተብሎ ተገምቷል፡፡
 
ፖሊሲ ኢንዱስትሪውን ቀይሮታል
የአውሮፓ ሕብረት ከደን ምንጣሮ ነጻ ምርት ደምብ  እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር ከዲሴምበር 20/2026 ጀምሮ የተሰበሰበ  የቡና ዱካ እና ከደን ነጻ ዳታ የቡና ንግድ ሁኔታውን የሚወስን ይሆናል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ፡-
Ø  የኬንያ ቡና ACT 2026 ተጨማሪ የቡና ቻናሎችን (መስመሮችን) ዘርግታለች
Ø  ታንዛኒያ የቡና ዋጋ ቤንች ማርክ አስተዋውቃለች
Ø  የብራዚል-ዩኤስ የንግድ ፖሊሲ ዓለማቀፍ የቡና ፍሰት ሁኔታ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን ቀጥሏል፡፡
 
የ2026 የቡና ዋጋዎች የሚያበቁት መቼ ነው?
የነሐሴ አጋማሽ ደራጃዎች፡-
የዓለም ዓቀፍ የንግድ ድርጅት፡-  ለ0.5 ኪሎ ቡና 285 ሳንቲም
የኒዮርክ አረቢካ፡- ለ0.5 ኪሎ ቡና ከ3.15 -3.20 ዶላር
 
የቡና ታሪክ እልፍ ብሏል
ቡና የሸቀጥ ታሪክ ያለው ከመሆን ተሸግሯል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቡና የአየር ንብረት መቋቋም፣ የዱካ ሁኔታ፣ ዳታ፣ የገበያ ተደራሽነት፣ ታማኝ ግንኙነት፣ ሎጂስቲክ፣ የእሴት ስርጭት፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ደንቦች፣ የጥራት ጉዳዮች የሚመለከቱት ሆኗል፡፡
ስለሆነም በቀጣይ ምን ያህል ቡና ተመረተ ብቻ የቡና ሁኔታዎችን አይወስንም፤ ይልቅ የዓለም የቡና እሴት ሰንሰለትን ውስጥ ብስለት በተሞላበት መልኩ ግንኙነት መፍጠር፣ ግብይት ማካሄድ እና ማስተዳደር ወሳኞች ሁኔታዎች ይሆናሉ፡፡
 
ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ቡና ሁኔታ እንዴት ታዩታላችሁ?
ሐሳባችሁን በኮሜንት መስጫ ላይ ያጋሩን፡፡
 
ምንጭ፡- ዓለማቀፍ የስፔሻሊቲ ቡና ማኅበር ሊንክድኢን ላይ እንደፖሰተው
https://lnkd.in/p/eAPtxm4b
ጥንቅር፡- በአሸናፊ ጌታሁን
LinkedIn
2026 Coffee Market Outlook: Volatility, Recovery & Transformation | M. Okan O. posted on the topic | LinkedIn
2026 Coffee: A Year of Volatility, Recovery & Transformation 2026 is already proving to be another pivotal year for the global coffee industry. As the new harvest season begins, let’s take a look at what 2026 has shown us so far — and what it could mean…
August 14, 2026 2.8K 16