ኮሎምቢያ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ገጠማት!!
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 10 ቀን 2026 በኮሎምቢያ ቾኮ (Chocó) ግዛት ሳን ሆሴ ዴል ፓልማር (San José del Palmar) መንደር አቅራቢያ 7.4 ሬክተር ስኬል የሚለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። አደጋው በዚህ ክፍለ ዘመን በሀገሪቱ ከተመዘገቡት የመሬት መንቀጥቀጦች ሁሉ እጅግ ሀይለኛው ሲሆን፣ እስካሁን ከ169 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ እየተነገረ ነው፡፡
አደጋው ዋና ዋና የቡና አምራች ክልሎችን (ሪሳራልዳ፣ ቫሌ ዴል ካውካ፣ ካልዳስ፣ አንቲዮኪያ፣ ቾኮ እና ኪንዲዮ) በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቷል። የብሔራዊ የቡና አምራቾች ፌዴሬሽን (FNC) ዋና ስራ አስኪያጅ ዠርማን ባሃሞን (Germán Bahamón) እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ብቸኛው እና ዋነኛው ቅድሚያ የሚሰጠው የሰው ህይወት ማዳን መሆኑን ገልጸው፣ የቡና ምርት መዋቅሮችን የመልሶ መገንባት ስራ ከመንግስት ጋር በመሆን በሂደት እንደሚከናወን አስታውቀዋል።
በዋና ዋና መንገድ መሰረተ ልማቶች እና በሀገሪቱ ዋና የወደብ ከተማ ቡኤናቬንቱራ (Buenaventura) ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት የኮሎምቢያ የቡና ኤክስፖርት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ቆሟል። የኮሎምቢያ የቡና ላኪዎች ማህበር (Asoexport) ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ጎሜዝ እንደገለጹት፣ የወደብ እና የመንገድ አገልግሎቶች መቼ እንደሚከፈቱ የታወቀ ጊዜ የሌለ ሲሆን፣ የኤሌክትሪክ እና የኮሙኒኬሽን መቋረጥም በቡና ማቀናበሪያ ተቋማት ስራ ላይ እንቅፋት ፈጥሯል ተብሏል።
ምንጫችን ግሎባል ኮፊ ሪፖርት ነው!!
አገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር በተለየ በቡናው ዘርፍ ያላት የጋራ ትብብር ቀላል ባለመሆኑ በደረሰው ሰብአዊም ሆነ የንብረት ጉዳት ባለስልጣን መ/ቤቱ በዚህ አጋጣሚ ሀዘኑን ይገልጻል፡፡

August 12, 2026 2.9K 5