ያን ጉባኤ አያለዉ ያንንኑ ሙሉ ሰዉ
ሁሉ በአንድነት ገብቶ ወደታነፀዉ
ልቤ ለዚያ ፅኑ ነዉ ዛሬ እንኳን ባይደላዉ
አልከፋም በዚያ ሁሉን እረሳለዉ
1. ተጠላልፎ የወደቀዉ
የምድር ህይወት ድካም ነዉ
ማን ተስፋ ሊያረገዉ
ነገዉ እንፋሎት ነዉ
አሄ በጥቂት መዛሌ
ደክሜ መሰበሬ
ተስፋዬ በላይ እንጂ
በዚ አይደለም ክብሬ
ከቀናቴ ደመና ከፍ ልበልና
ልታገስ ደጅህን ልጥና
ተስፋዬ ቀርቧልና
ዉርደት ሀጢአት ዉድቀት
ከቶም የሌለበት
ዉዴ ራስ የሆነበት
ናፍቆኛል ያ ሙሉ ቤት
ያን ጉባኤ አያለዉ...............
2. ስጋ ተዋርዶ ሲዘራ
መች ይመስላል ሚነሳ
እንኳን ሰዉ ግን ላይከብር
አይቀርም ዛፍ እንስሳ
ሞት እንደዉ ልማዱ ነዉ
ስንቱን ከኛ ወሰደዉ
ያ ቀን በደጅ ነዉ
ትንሳኤን የያዘዉ
በጌታ ያመነ
ሰዉ ቢሞት መች ጎደለ
ዘላለም በታመነ
በእርሱ እቅፍ ታደለ
ያንን ቀን የናፈቀ
ዘይቱንም የሰነቀ
ይዘጋጅ የጠበቀ
ባየር ላይ ተነጠቀ
ያን ጉባኤ አያለዉ .............
3. አንዳንዴ ብርታት ይከዳል
ሁለንተናም ይጎዳል
ስጋ ነፍስን ስትወጋ
መንፈስ ይጠመዳል
ያን ጊዜ ከሳሽ ይቀርባል
ፍላፃዉን ይልካል
ገና በንብርክክ ሳለዉ
አባቴ ፈጥኖ ይደርሳል
ይኸዉ ዘምራለዉ
ሚዋጋልኝ እርሱ ነዉ
በቅፉ እንዳለዉ
ሩጫዬን ጨርሳለዉ
አይዞኝ ጥቂት ጊዜ ነዉ
ስጋዬም መታደሱ ነዉ
አባቴን የማየዉ ወይ ዛሬ ወይ ነገ ነዉ
ያን ጉባኤ አያለዉ ............
3August 18, 2026 66