ጎግል ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው 10 ሺ ተጠቃሚዎች የደህንነት ቁልፍ ሊሰጥ ነው ========================== በሳይበር ምህዳሩ ዘርፍ ከፍተኛ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት በሃከሮች ዋና ኢላማ እየተደረጉ ከመምጣታቸው አንጻር ጎግል በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ለእነዚህ ተጠቃሚዎቹ የማስጠንቀቂያ መልዕክት እና አድቫንስ ፐሮቴክሽን ፕሮግራም (APP) የተባለውን የቅርብ ጊዜ የደህንነት ሲስተም እንዲተገብሩ ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁንና በቅርብ ወራት ውስጥ ከፍተኛ ተከታይ ባላቸው የፖለቲካ መሪዎች፣ የሰብኣዊ መብት አክቲቪስቶች እና ሌሎች ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ባለባቸው አካላት ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ የሳይበር ወንጀል፤ ሌሎች የደህንነት አሰራረሮችን ለመተግበር እያስገደደው እንደመጣ ያስታወቀው ጎግል አሁን ላይ 10ሺ ለሚጠጉ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው ተጠቃሚዎች አዲስ የደህንነት ቁልፍ ሊሰጥ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ በ2021 ብቻ ውስብስብ የሳይበር ጥቃት እየተፈፀማባቸው የሚገኙ እና የሃገር መንግስታት ድጋፍ የሚደርጉላቸው ሃከሮች የሚሞክሩትን የሳይበር ጥቃት ለማክሸፍ አድቫንስ ፐሮቴክሽን ፕሮግራም የተባለውን የደህንነት ስርዓት ተጠቃሚዎች እንዲተግበሩ ጎግል ሲሳስብ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ይህንን ሳያደርጉ የቆዩና በመስከረም ወር የማጣራት ሂደት ብቻ ከፍተኛ የሳይበር ሙከራ በተደረገባቸው 14 ሺ በላይ የጂሜል ተጠቃሚዎች የማስጠንቀቂያ መልክት መላኩን የተናገሩት በድርጅቱ ውስጥ የስጋት ትንተና ቡድን ሃላፊ የሆኑት ሚስተር ሃንትሊ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው አካላት የኦንላይን አጠቃቀማቸው ላይ የሚታየውን ተጋላጭነት በፍጥነት እንዲሞሉ ተዳጋገሚ ማሳሰቢያ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡ ጎግል አሁን ላይ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው 10 ሺ ተጠቃሚዎች የሚያቀርበው የደህንነት ቁልፍ በኮምፒውተራቸው ላይ በሚሰኩ የሃርድዌር ዩኤስቢ መሳሪዎች አማካኝነት የሚሰሩ ሲሆን በዋናነት የተጠቃሚዎችን አካውንት ለመጥለፍ የሚያስችሉ የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችን በሚገባ ለመከላከል የሚግዝ ነው፡፡ ታይታን ብሎ የሰየመውን የድህንነት ቁልፉ ለተጠቃሚዎች ለማሰራጨት ጎግል ከብዙ የቴክኖሎጂ ድጅቶች ጋር እየሰራ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ከዚህ በፊት ከከቀረቡት ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (two-factor authentication) አሰራሮች በተጨማሪ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው 10 ሺ ተጠቃሚዎች የቀረበው ይህ የደህንነት ቁልፍ እየተባባሰ የመጠውን የሳይበር ወንጀል ለመከላከል በእጅጉ እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡ https://www.techradar.com/news/google-will-give-free-security-keys-to-high-risk-users
TechRadarGoogle will give free security keys to 'high risk' usersSearch giant plans to distribute 10,000 security keys throughout 2021Dire Dawa Education Bureau: post #182 — TG.ME
October 12, 2021 12.8K 3