Dire Dawa Education Bureau: post #179 — TG.ME

የኮሌጅ ዲግሪን በ6 ወር የምስክር ወረቀት ለመተካት ያሰበው ጎግል ****************** የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ጎግል ከኮሌጅ ዲግሪ ይልቅ የስድስት ወር ርዝማኔ ያላቸውን ኮርሶች በመስጠት ሰራተኞችን ለመቅጠር ማቀዱን አሳውቋል፡፡ ኩባንያው አራት አመት በሚረዝም የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ስራ ለመቀጠር ከሚወዳደሩ ሰዎች ይልቅ ድርጅቱ የሚያዘጋጀውን የስድስት ወር ኮርስ በማጠናቀቅ ምስክር ወረቀት ያላቸውን ሰዎች ተመራጭ እንደሚያደርግ ተናግሯል፡፡ ለዚህ ስልጠና የሚያስፈልገው ክፍያ እስካሁን ይፋ ባይደረግም ከዚህ ቀደም ድርጅቱ ከሚሰጣቸው ስልጠናዎች ዋጋ በመነሳት እስከ 300 የአሜሪካን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ድርጅቱ 100 ሺህ የሚደርሱ የትምህርት እድሎችን እንዳመቻቸ ያሳወቀ ሲሆን በትምህርታቸው የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ተማሪዎች ኮርሱን ቢወስዱ ከፍተኛ ከፋይ በሆኑ ተቋማት የመቀጠር እድላቸውን እንደሚያሰፋላቸው ተነግሯል፡፡ በዚህ የስድስት ወር ፕሮግራም ውስጥ እንደ መረጃ ትንተና እና የፕሮጀክት አስተዳደር ያሉ ኮርሶች ተካተውበታል፡፡ እነዚህ የስልጠና አይነቶች የጎግል ተቀጣሪ የሆኑ ሙያተኞችን ክህሎት ለማዳበር ታስበው የተዘጋጁ ሲሆን ሰራተኞቹ ከስልጠናዎቹ አዳዲስ ክህሎቶችን እንደሚማሩባቸው የተናገሩት የጎግል አለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ኬንት ዎከር አክለውም በስልጠናዎቹ የሚሳተፉ ሰዎች ስራ ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት እጅግ እንደሚቀልላቸው ገልጸዋል፡፡ ለስልጠናዎቹም ምንም አይነት ዲግሪም ሆነ የስራ ልምድ አይጠየቅም ተብሏል፡፡ የዚህ ፕሮግራም አላማ እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ በተለይ በአሜሪካ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ለሁሉም ተደራሽ አለመሆንና ኢኮኖሚያዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ የግድ የኮሌጅ ዲግሪ አስፈላጊ ባለመሆኑ ሲሆን በተለይ በአጫጭር ስለጠናዎች ሊሰሩ የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት አራትና አምስት አመት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሆኖ ጊዜን፣ ገንዘብንና ጉልበትን መጨረስ አያስፈልግም በሚል እሳቤ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ምንጭ፡ iflscience ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/policy/google-plan-to-replace-the-need-for-college-degrees-with-sixmonth-certificates/?fbclid=IwAR3kngUgDi-ItPY9gtQRZ4BrRzu12BQEbopIlOuUspLuXdRE2JPK18Xaf5A

IFLScienceGoogle Plan To Replace The Need For College Degrees With Six-month CertificatesThe tech giant Google has announced they will begin accepting Google Learning Certificates in place of college degrees, offering six-month courses for pros
May 2, 2021 10.3K 1