Change your Life: post #1981 — TG.ME

መጥፎ ሰዎች 😈 አንዳንድ ሰዎች በመጥፎ ባህርያቸው የእናንተን መልካም ምግባር ለመቀየር ሊፈትኗችሁ ይችላሉ። ባጎረሳችሁ ይነክሷችኋል። ለእነሱ መልካም ለማድረግ ስትደክሙ ፣ ስማችሁን በመጥፎ ያነሳሉ። ትንሽ ቆሞ ብላችሁ ስታስቡት🤔 'ምን አገባኝ? እኔ አልጎዳ ፣ የራሳቸው ጉዳይ!' ልትሉና የእናንተን መልካም ስብዕና ልትተዉ ትችላላችሁ። ያ መሆን ግን የለበትም። የእናንተ መልካም ምግባር በሰው መልካም/መጥፎ ምግባር ላይ መመስረት የለበትም። የራሳችሁን ህይወት/ ስነምግባር ራሳችሁ ወስኑ በሰዎች ይወሰን ዘንድ አትፍቀዱ። .

May 12, 2026 1.9K 7